The big bang theory ላይ የተሳለው ገፀ ባህሪ ሼልደን ኩፐር ለአስፐርገር ሲንድረም ጥሩ ማሳያ ይሆናል፡፡ እናቱ ሁለቴ የአእምሮ ሀኪም ጋር ወስዳው ምንም የአእምሮ እክል የለብህም ቢባልም የሚያሳያቸው ፀባዮች አስፐርገር ሲንድረም እንዳለበት ይጠቁማሉ፡፡ አስፐርገር ሲንድረም ሰዎች አለምን የሚያዩበትን መንገድ እንዲሁም ከሰው ጋር የሚኖራቸውን ግንኙኘት የሚለውጥ ከኦቲዝም ህብር ህመሞች አንዱ ነው፡፡ እንደሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች የሌሎች ሰዎችን ስሜት ለመረዳት መቸገር፣ ለውጥ አለመፈለግ፣ ተመሳሳይ ነገሮችን ደጋግሞ መስራት ይታይባቸዋል፡፡ ከሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች በተሻለ የቋንቋ ክህሎታቸው እና አጠቃላይ የመገንዘብ /የመረዳት ችሎታቸው (ማህበራዊ ግንኙነትን ሳይጨምር) ጥሩ ነው፡፡ የተሻለ የመገንዘብና የንግግር ችሎታ ቢኖራቸውም ቋንቋን ሚረዱበት መንገድ የተለየ ነው፡፡ በተለይም ሽሙጥ፣ ስላቅን ለመረዳት ይቸገራሉ፡፡ ምሳሌያዊ አነጋገሮችን እንደወረደ በጥሬው ነው የሚረዱት፡፡ አስፐርገር መገለጫው ከሰው ሰው ስለሚለያይ መኖሩን በቀላሉ ለመለየት ያስቸግራል፡፡ህምናው በዋናነት ቶሎ መለየትና የማህበራዊ ክህሎት ስልጠና ነው፡፡ መልካም ጊዜ! ዶ/ር ዮናስ ላቀው
* ምርጫ አይደለም፡፡
* ትኩረት መፈለግ አይደለም፡፡)
* ስድብ ወይም ቅጽል አይደለም፡፡
* ሰበብ አይደለም፡፡
* ስንፍና አይደለም፡፡
* በአንዴ ውጥት የሚሉበት ነገር አይደለም፡፡ * ወንጀል አይደለም፡፡
* ደካማ መሆን ማለት አይደለም፡፡
* ውሸት ወይም በአእምሮ የተፈጠረ አይደለም፡፡
* ቀልድ ወይም የሚያስቅ ነገር አይደለም፡፡
* ዘመናዊ ክስተት አይደለም፡፡
* ሁሉም ሰው የሚያልፍበትት የህይወት ደረጃ አይደለም፡፡
* የማግለያ ምክኒያት መሆን የለበትም፡፡ (ሁላችንም ላይ ሊከሰት ይችላል፡፡)
* ሁሉም ሰው ላይ ተመሳሳይ አይደለም፡፡
* የሚያስከትለው ተጽእኖ ከአካላዊ ህመሞች ያነሰ አይደለም፡፡
ከ Mental health and invisible illness resources የተተረጎመ
መልካም ጊዜ!
Emperor Casino: Casino | Slots & Live Dealers - Shoot
ReplyDeleteEnjoy the most septcasino exciting online casino games 제왕카지노 at Immortal Casino! 카지노사이트 Play Live Dealers, Free Spins, Cash Back, Multiplier, Deuces Wild and more.