The big bang theory ላይ የተሳለው ገፀ ባህሪ ሼልደን ኩፐር ለአስፐርገር ሲንድረም ጥሩ ማሳያ ይሆናል፡፡ እናቱ ሁለቴ የአእምሮ ሀኪም ጋር ወስዳው ምንም የአእምሮ እክል የለብህም ቢባልም የሚያሳያቸው ፀባዮች አስፐርገር ሲንድረም እንዳለበት ይጠቁማሉ፡፡ አስፐርገር ሲንድረም ሰዎች አለምን የሚያዩበትን መንገድ እንዲሁም ከሰው ጋር የሚኖራቸውን ግንኙኘት የሚለውጥ ከኦቲዝም ህብር ህመሞች አንዱ ነው፡፡ እንደሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች የሌሎች ሰዎችን ስሜት ለመረዳት መቸገር፣ ለውጥ አለመፈለግ፣ ተመሳሳይ ነገሮችን ደጋግሞ መስራት ይታይባቸዋል፡፡ ከሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች በተሻለ የቋንቋ ክህሎታቸው እና አጠቃላይ የመገንዘብ /የመረዳት ችሎታቸው (ማህበራዊ ግንኙነትን ሳይጨምር) ጥሩ ነው፡፡ የተሻለ የመገንዘብና የንግግር ችሎታ ቢኖራቸውም ቋንቋን ሚረዱበት መንገድ የተለየ ነው፡፡ በተለይም ሽሙጥ፣ ስላቅን ለመረዳት ይቸገራሉ፡፡ ምሳሌያዊ አነጋገሮችን እንደወረደ በጥሬው ነው የሚረዱት፡፡ አስፐርገር መገለጫው ከሰው ሰው ስለሚለያይ መኖሩን በቀላሉ ለመለየት ያስቸግራል፡፡ህምናው በዋናነት ቶሎ መለየትና የማህበራዊ ክህሎት ስልጠና ነው፡፡ መልካም ጊዜ! ዶ/ር ዮናስ ላቀው
ሁለት ሰዎች የፈለገ ቢዋደዱ የፍቅር ግንኙነታቸው እንዲዘልቅ ትልቅ ጥረት ይጠይቃል፡፡ በዚህ ጥረት ውስጥ የፍቅር ቋንቋ ጉልህ ድርሻ ይይዛል፡፡ የፍቅር ተጣማሪ የሚጠብቀውንና የሚፈልገውን መረዳት የፍቅር ህይወትን ከማሻሻሉ ጋር ተያይዞ በአጠቃላይ ጥሩ ስሜት፣ ደስታና በስራ ላይ ውጤታማነት ያመጣል፡፡
ሰዎች ፍቅራቸውን የሚገልፁባቸው ወይም የተጣማሪያቸውን ድርጊት የሚረዱባቸው የተለያዩ መንገዶች አሉ፡፡ ጠቅለል ተደርገው በአምስት ሊመደቡ ይችላሉ፡፡ እነሆ፦
- የፍቅር ቃላትየፍቅር ቃላት ለሚመርጡ ሰዎች ‹‹እወድሃለሁ›› ወይም ‹‹እወድሻለሁ›› የሚሉት ቃላት ትልቅ ትርጉም አላቸው፡፡ በተጨማሪም ከተጣማሪያቸው ለሚሰነዘር አድናቆት ትልቅ ቦታ ይሰጣሉ፡፡ቃላት የከበረ ዋጋ አላቸው፡፡ በተቃራኒው አሉታዊ ወይንም ስድብ የሚመስል ቃላት ይጎዳቸዋል፡፡ በቀላሉ ይቅር ለማለት ይቸገራሉ፡፡
- ጥሩ ጊዜ
ይህ የፍቅር ቋንቋ ለተጣማሪ ያልተከፋፈለ ትኩረት ስለመስጠት ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ከቃላት ይልቅ የተጣማሪያቸውን ጊዜና ያልተከፋፈለ ትኩረት ማግኘት ጥሩ ስሜት ይፈጥርላቸዋል፡፡ በተቃራኒው የተከፋፈለ ትኩረት ፣ቀጠሮ መሰረዝና አለመደመጥ ያስከፋቸዋል፡፡
- ስጦታ መቀበል
ለአንዳንድ ሰዎች የመወደድ ስሜት እንዲሰማቸው ስጦታዎች ያስፈልጋሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ቁሳዊያን ናቸው ማለት አይደለም፡፡ ከስጦታው ይበልጥ ስጦታን ለመስጠት የተደረገው ሀሳብ በስጦታ ሰጪው ያላቸውን ቦታ ያረጋግጥላቸዋል፡፡
- ተግባራዊ እገዛ
ለእነዚህ ሰዎች ድርጊቶች ከቃላት ይበልጥባቸዋል፡፡ ተጣማሪያቸው እየለፉ ያለበትን አስቸጋሪ ጉዞ ተረድተው በተግባር ቢያግዟቸው ይመርጣሉ፡፡ ለእነሱ ተግባራዊ እገዛ የማሰብና የፍቅር መገለጫ ነው፡፡ ይህንን ቋንቋ የሚጠቀመው ሰዎች ቃላቸውን ከማይጠብቁና በነሱ እይታ 'ሰነፍ' ብለው ካሰቡት ሰው ጋር ለመዝለቅ ይቸግራቸዋል፡
- አካላዊ ንክኪ
ለእነዚህ ሰዎች ተገቢ ከሆነ አካላዊ ንኪኪ የተሻለ ፍቅር የሚገለፅበት መንገድ የለም፡፡ 'መኝታ ቤት' ውስጥ ብቻ ሳይሆን በእለት ተእለት ማለትም፡- እጅ መያያዝ፣መተቃቀፍ፣ መሳሳም ወይም ማንኛውም አይነት የፍቅር ንኪኪ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህን አይነት የፍቅር ቋንቋ የሚጠቀሙ ሰዎች በየቦታው ይሳሳማሉ ማለት ሳይሆን ተገቢው ንኪኪ ጥሩ ስሜት ይፈጥርባቸዋል ለማለት ነው፡፡ በተቃራኒው ማንኛውንም አይነት አካላዊ ጥቃት አይታገሱም፡፡
ለማጠቃለል ፡- አንድ ሰው ወይም ተጣማሪው አንዱን አይነት የፍቅር ቋንቋ ይመርጣል ማለት ሌሎችን መግለፅ ማቆም አለብን ማለት አይደለም፡፡ አንዱን ብንመርጥም ሌሎቹም ያስፈልጋሉ፡፡
ከዶ/ር ጌሪ ቻፕማን The five love languages የተተረጎመ
Comments
Post a Comment