The big bang theory ላይ የተሳለው ገፀ ባህሪ ሼልደን ኩፐር ለአስፐርገር ሲንድረም ጥሩ ማሳያ ይሆናል፡፡ እናቱ ሁለቴ የአእምሮ ሀኪም ጋር ወስዳው ምንም የአእምሮ እክል የለብህም ቢባልም የሚያሳያቸው ፀባዮች አስፐርገር ሲንድረም እንዳለበት ይጠቁማሉ፡፡ አስፐርገር ሲንድረም ሰዎች አለምን የሚያዩበትን መንገድ እንዲሁም ከሰው ጋር የሚኖራቸውን ግንኙኘት የሚለውጥ ከኦቲዝም ህብር ህመሞች አንዱ ነው፡፡ እንደሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች የሌሎች ሰዎችን ስሜት ለመረዳት መቸገር፣ ለውጥ አለመፈለግ፣ ተመሳሳይ ነገሮችን ደጋግሞ መስራት ይታይባቸዋል፡፡ ከሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች በተሻለ የቋንቋ ክህሎታቸው እና አጠቃላይ የመገንዘብ /የመረዳት ችሎታቸው (ማህበራዊ ግንኙነትን ሳይጨምር) ጥሩ ነው፡፡ የተሻለ የመገንዘብና የንግግር ችሎታ ቢኖራቸውም ቋንቋን ሚረዱበት መንገድ የተለየ ነው፡፡ በተለይም ሽሙጥ፣ ስላቅን ለመረዳት ይቸገራሉ፡፡ ምሳሌያዊ አነጋገሮችን እንደወረደ በጥሬው ነው የሚረዱት፡፡ አስፐርገር መገለጫው ከሰው ሰው ስለሚለያይ መኖሩን በቀላሉ ለመለየት ያስቸግራል፡፡ህምናው በዋናነት ቶሎ መለየትና የማህበራዊ ክህሎት ስልጠና ነው፡፡ መልካም ጊዜ! ዶ/ር ዮናስ ላቀው
አሁን እንዳለንበት ጊዜየሀይማኖት አስፈላጊነት አጠያያቂ የነበረበት ጊዜ የለም፡፡ ለረጅም አመታት ሀይማኖትና የአእምሮ ህክምና 'ዘይትና ውሃ' ተደርጎ ሲወሰድ ቆይቷል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሀይማኖትና የመንፈሳዊነት አስፈላጊነት ግንዛቤ እያደገ መጥቷል ፡፡ ከአእምሮ ጤና (mental wellness) ጋር ያለው ግንኙነት በጥቂቱ እንሆ፡-
ሀይማኖት ፡- የተደራጀ በህብረት የሆነ የእምነት መንገድ ሲሆን ተመሣሣይ እምነት ከሚጋሩ ሰዎች ጋር(በይበልጥ) ጥሩ ግንኙነት እንዲኖር ይረዳል፡፡ አንድ ትልቅ ቤተሰብ (a family of friends) እንደማለት ነው ፡፡በሀዘን በችግር ጊዜ የእምነት ተከታዮች የሚያደርጉት የሞራል (emotional) ወይም ቁሳዊ(instrumental) እገዛ ለድብርትና ለጭንቀት የመጋለጥ እድልን በእጅጉ ይቀንሳል፡፡
ሁሉም ሀይማኖቶች ሱስ አምጪ ነገሮችን አያበረታቱም ፡፡ ይኸውም ከሱስ ጋር ተያይዞ ከሚመጣ የአእምሮ ህመም ይከላከላል፡፡ ሀይማኖት ራስን የማጥፋት እድልን በእጅጉ ይቀንሳል፡፡
ሁሉም ሀይማኖቶች ሱስ አምጪ ነገሮችን አያበረታቱም ፡፡ ይኸውም ከሱስ ጋር ተያይዞ ከሚመጣ የአእምሮ ህመም ይከላከላል፡፡ ሀይማኖት ራስን የማጥፋት እድልን በእጅጉ ይቀንሳል፡፡
መንፈሳዊነት ፡- በግለሰብ ደረጃ ያለ እምነትና መንፈሳዊ መረዳት ሲሆን አንድ ሰው የሀይማኖት ተከታይ ሣይሆን መንፈሳዊ ሊሆን ይችላል፡፡መንፈሳዊ የሆኑ ሰዎች ራሣቸውን የሚያውቁ፣ ራሳቸውንና ሌላውን የሚቀበሉና ይቅርታ የሚያደርጉ ስለሆኑ የተረጋጉ ናቸው፡፡
ከጭንቀት ይልቅ መፍትሄ፣ ከሀሜት ይልቅ ምክር፣ ከመጥፎ ጎን ይልቅ ጥሩ ጎንን ማየት ስለሚመርጡ ደስተኞች ናቸው፡፡ በተጨማሪም መንፈሣዊነት ሰዎች በመሆናችን ብቻ የሚያስጨንቁን (existential anxieties) ማለትም ፡፡ ‹‹የሕይወት ትርጉም ምንድነው?›› ‹‹ዓለማዬ ምንድን ነው?›› ‹‹ ከሞት በኃላ ምን አለ?›› ለሚሉት ጥያቄዎች በቂ ምላሽ ስለሚሰጥ የውስጥ ስላምና መረጋጋት ያላብሳል ፡፡
ለማጠቃለል ሀይማኖትና መንፈሣዊነት ሰዎች ከራሳቸው ከፍ ያለ ሕይወት እንደዲኖሩ ይረዳል፡፡ እንዲሁም የሕይወትን ጫና በጥንካሬና በሰከነ አእምሮ ለመቋቋም ፣ እያለፉ ያለበትን ጉዞ ትርጉም እንዲኖረውና ወደፊት ብሩሕ ተስፋ እንዳለ ያስረዳል፡፡
ሀይማኖትና የአእምሮ ህክምና በሌላ ጊዜ ይቀርባል፡፡
Comments
Post a Comment