The big bang theory ላይ የተሳለው ገፀ ባህሪ ሼልደን ኩፐር ለአስፐርገር ሲንድረም ጥሩ ማሳያ ይሆናል፡፡ እናቱ ሁለቴ የአእምሮ ሀኪም ጋር ወስዳው ምንም የአእምሮ እክል የለብህም ቢባልም የሚያሳያቸው ፀባዮች አስፐርገር ሲንድረም እንዳለበት ይጠቁማሉ፡፡ አስፐርገር ሲንድረም ሰዎች አለምን የሚያዩበትን መንገድ እንዲሁም ከሰው ጋር የሚኖራቸውን ግንኙኘት የሚለውጥ ከኦቲዝም ህብር ህመሞች አንዱ ነው፡፡ እንደሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች የሌሎች ሰዎችን ስሜት ለመረዳት መቸገር፣ ለውጥ አለመፈለግ፣ ተመሳሳይ ነገሮችን ደጋግሞ መስራት ይታይባቸዋል፡፡ ከሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች በተሻለ የቋንቋ ክህሎታቸው እና አጠቃላይ የመገንዘብ /የመረዳት ችሎታቸው (ማህበራዊ ግንኙነትን ሳይጨምር) ጥሩ ነው፡፡ የተሻለ የመገንዘብና የንግግር ችሎታ ቢኖራቸውም ቋንቋን ሚረዱበት መንገድ የተለየ ነው፡፡ በተለይም ሽሙጥ፣ ስላቅን ለመረዳት ይቸገራሉ፡፡ ምሳሌያዊ አነጋገሮችን እንደወረደ በጥሬው ነው የሚረዱት፡፡ አስፐርገር መገለጫው ከሰው ሰው ስለሚለያይ መኖሩን በቀላሉ ለመለየት ያስቸግራል፡፡ህምናው በዋናነት ቶሎ መለየትና የማህበራዊ ክህሎት ስልጠና ነው፡፡ መልካም ጊዜ! ዶ/ር ዮናስ ላቀው
ምቀኝነት አንድ ሰው እንዲኖረው የሚፈልገውን ችሎታ፣ ስኬት፣ ንብረት...ወዘተ ሌላ ሰው ሲኖረው የሚፈጠር ስሜት ሲሆን መሰረታዊ ከሆኑት ስሜቶቾ አንጻር ሲታይ የንዴትና የሀዘን ድብልቅ ነው፡፡
ሌላ ሰው የተሻለ ነገር ሲሰራ ወይም ሲኖረው ሁለት አይነት ስሜት ሊፈጥር ይችላል፡፡ አድናቆት ወይም ምቀኝነት፡፡ አድናቆት የሌላውን መሻል በትህትና መቀበል ሲሆን፤ ምቀኝነት በንዴት ላለመቀበል መሞከር ነው፡፡
- ማን ማንን ይመቀኛል? ሰዎች የሚመቀኙት ከእነሱ ጋር ተቀራራቢ ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎችን ነው፡፡ ጓደኛ፣ ጎረቤት፣ የስራ ባልደረባ ...ወዘተ፡፡ ጫማህን የሚጠርገው ሊስትሮ አንተ የተሻለ ኑሮ ስራ ስላለህ ምቀኝነት አይሰማውም፡፡ ይልቁንም አጠገቡ ያለ ሌላ ሊስትሮ የተሻለ ገንዘብ ሲያገኝ ነው ምቀኝነት የሚሰማው፡፡ ጎረቤትህ የተሻለ ቤት ስትሰራ ምቀኝነት ይሰማው ይሆናል እንጂ አላሙዲን አዲስ ህንፃ ቢሰራ ምንም ስሜት አይፈጥርበትም፡፡ በአጠቃላይ ምቀኛ ከሩቅ አይመጣም፡፡
- ምቀኝነት ወይስ ቅናት? አንዳንድ ሰዎች ሁለቱን ሲያቀያይሩ ይስተዋላል፡፡ ነገር ግን የተለያዩ ስሜቶች ናቸው፡፡ ቅናት ቦታ የምንሰጠው ነገር እንዳይወሰድብን ስንፈራ የሚፈጠር ስሜት ሲሆን እንዳይወሰድ የምንፈልገውን ነገር ለመጠበቅ ጥረት እንድናደርግ የሚገፋፋ ነው፡፡ በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ሲፈጠር ሰዎች ረጅም (አንዳንድ ጊዜ ከልክ ያለፈ) ርቀት እንዲሄዱ ያደርጋል፡፡ ምቀኝነት የሚፈጠረው አንድ ሰው ቢኖረው የሚመኘውን (ነገር ግን የሌለውን) ሌላ ሰው ሲኖረው የሚፈጠር ሲሆን ልዩነቱን ለማጥበብ ሌላውን ካለበት ለማውረድ ወይም ራስን ከፍ ለማድረግ እንዲጣጣር ይገፋፋል፡፡ "አላውቃትም እንዴ እንዴት እንደነበረች..." "እኔ ገንዘብ ሰጥቼው አይደል ስራ የጀመረው፡፡" የመሳሰሉት
- የምቀኝነት ስሜትን እንዴት መከላከል ይቻላል? የሰው ልጅ ማህበራዊ በመሆኑ የትኛውም ደረጃ ላይ ቢኖር ራሱን ከሌሎች ጋር ማነጻጻሩ አይቀርም፡፡ ይህም መጠኑ ቢለያይም የምቀኝነት ስሜት ሊፈጥር ይችላል፡፡ የምቀኝነት ስሜት ከባድ ሰነልቦናዊ ህመም ይፈጥራል፡፡ ሁሉም ሰው የየራሱ ስኬት የየራሱ ውጣውረድ ውስጥ እንደሚያልፍ መረዳት የምቀኝነት ስሜትን ይቀንሰዋል፡፡ ፌስ ቡክ ላይ ከፍቅረኛዋ ጋር ስትዝናና ፓስት ታድርግ እንጂ ከዛ በፊት ለሁለት ቀናት የተኳረፉትን ፓስት አላደረገች ይሆናል፡፡ ስለደረሰበት ትልቅ ደረጃ ሲነግረን ስራ ላይ ሲያተኩር ከቤተሰቡ ጋር ብዙ ጊዜ እንደማያሳልፍ አልነገረን ይሆናል፡፡ የምቀኝነት ስሜትን ሌላውን ዝቅ ለማድረግ ከማዋል እራስን ለማሻሻል መጠቀም ይቻላል፡፡
አንድ ሰው ሲመቀኘን ከሱ በየሆነ ነገር የተሻልን እንደሆንን እንደሚያስብ ማስታወስ ጥሩ ነው፡፡
ItisgoodItisgoo
ReplyDelete