The big bang theory ላይ የተሳለው ገፀ ባህሪ ሼልደን ኩፐር ለአስፐርገር ሲንድረም ጥሩ ማሳያ ይሆናል፡፡ እናቱ ሁለቴ የአእምሮ ሀኪም ጋር ወስዳው ምንም የአእምሮ እክል የለብህም ቢባልም የሚያሳያቸው ፀባዮች አስፐርገር ሲንድረም እንዳለበት ይጠቁማሉ፡፡ አስፐርገር ሲንድረም ሰዎች አለምን የሚያዩበትን መንገድ እንዲሁም ከሰው ጋር የሚኖራቸውን ግንኙኘት የሚለውጥ ከኦቲዝም ህብር ህመሞች አንዱ ነው፡፡ እንደሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች የሌሎች ሰዎችን ስሜት ለመረዳት መቸገር፣ ለውጥ አለመፈለግ፣ ተመሳሳይ ነገሮችን ደጋግሞ መስራት ይታይባቸዋል፡፡ ከሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች በተሻለ የቋንቋ ክህሎታቸው እና አጠቃላይ የመገንዘብ /የመረዳት ችሎታቸው (ማህበራዊ ግንኙነትን ሳይጨምር) ጥሩ ነው፡፡ የተሻለ የመገንዘብና የንግግር ችሎታ ቢኖራቸውም ቋንቋን ሚረዱበት መንገድ የተለየ ነው፡፡ በተለይም ሽሙጥ፣ ስላቅን ለመረዳት ይቸገራሉ፡፡ ምሳሌያዊ አነጋገሮችን እንደወረደ በጥሬው ነው የሚረዱት፡፡ አስፐርገር መገለጫው ከሰው ሰው ስለሚለያይ መኖሩን በቀላሉ ለመለየት ያስቸግራል፡፡ህምናው በዋናነት ቶሎ መለየትና የማህበራዊ ክህሎት ስልጠና ነው፡፡ መልካም ጊዜ! ዶ/ር ዮናስ ላቀው
ፎቢያ ለአንድ ነገር ወይም ሁኔታ ምክኒያታዊ ያልሆነ ከፍተኛ ፍርሀት ማለት ሲሆን የተወሰኑት እነሆ፦
• አኩሎፎቢያ (Achulophobia)- የጨለማ ፍርሀት
• አክሮፎቢያ (Acrophobia)- የከፍታ ፍርሀት
• አውቶፎቢያ (Autophobia)- የብቸኝነት ፍርሀት
• ክላስትሮፎቢያ (Claustrophobia)- ትፍግፍግ ያለ ቦታ ፍርሀት
• ሳይኖፎቢያ (Cynophonia)- የውሻ ፍርሀት
• ኢሉሮፎቢያ (Elurophobia)- የድመት ፍርሀት
• ጋሞፎቢያ (Gamophobia)- የትዳር ፍርሀት
• ሄሞፎቢያ (Hemophobia)-የደም ፍርሀት
• አያትሮፎቢያ (Iatrophobia)-የዶክተር ፍርሀት
• ሎኪኦፎቢያ (Lockiophobia)- የምጥና የመውለድ ፍርሀት
• ሙሶፎቢያ (Musophobia)- የአይጥ ፍርሀት
• ኔክሮፎቢያ (Necrophobia)- የሞተ ነገር ፍርሀት
• ኦፊዲኦፎቢያ (Ophidiophobia)- የእባብ ፍርሀት
• ፓቶፎቢያ (Pathophobia)- መታመምን መፍራት
• ፊሎፎቢያ (Philophobia)- የፍቅር ፍርሀት
• ፎቦፎቢያ (Phobophobia)- የፍርሀት ፍርሀት
• ፖለቲኮፎቢያ (Politicophobia)- የፓለቲከኞች ወይም የፓለቲካ ሂደት ፍርሀት
• ስኮሊኦኖፎቢያ (Scolionophobia)- የትምህርት ቤት ፍርሀት
• ትሪፓኖፎቢያ (Trypanophobia)- መርፌ የመወጋት ፍርሀት
• ታናቶፎቢያ (Thanatophobia)- የሞት ፍርሀት
• ዜኖፎቢያ (Xenophobia)- መጤ የሆነ ሰው ፍርሀት
ፎቢያዎች የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ጫና ሊያሳድሩ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ብቻዎን እንዳልሆኑ ያስታውሱ፡፡ ከመቶ ሰዎች አስሩ የሆነ አይነት ፎቢያ እንደሚኖራቸው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ያለ መድሀኒት በንግግር ህክምና (Psychotherapy, specifically behavioral therapy) ሊታከሙ ይችላሉ፡፡
መልካም ጊዜ!
Comments
Post a Comment