The big bang theory ላይ የተሳለው ገፀ ባህሪ ሼልደን ኩፐር ለአስፐርገር ሲንድረም ጥሩ ማሳያ ይሆናል፡፡ እናቱ ሁለቴ የአእምሮ ሀኪም ጋር ወስዳው ምንም የአእምሮ እክል የለብህም ቢባልም የሚያሳያቸው ፀባዮች አስፐርገር ሲንድረም እንዳለበት ይጠቁማሉ፡፡ አስፐርገር ሲንድረም ሰዎች አለምን የሚያዩበትን መንገድ እንዲሁም ከሰው ጋር የሚኖራቸውን ግንኙኘት የሚለውጥ ከኦቲዝም ህብር ህመሞች አንዱ ነው፡፡ እንደሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች የሌሎች ሰዎችን ስሜት ለመረዳት መቸገር፣ ለውጥ አለመፈለግ፣ ተመሳሳይ ነገሮችን ደጋግሞ መስራት ይታይባቸዋል፡፡ ከሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች በተሻለ የቋንቋ ክህሎታቸው እና አጠቃላይ የመገንዘብ /የመረዳት ችሎታቸው (ማህበራዊ ግንኙነትን ሳይጨምር) ጥሩ ነው፡፡ የተሻለ የመገንዘብና የንግግር ችሎታ ቢኖራቸውም ቋንቋን ሚረዱበት መንገድ የተለየ ነው፡፡ በተለይም ሽሙጥ፣ ስላቅን ለመረዳት ይቸገራሉ፡፡ ምሳሌያዊ አነጋገሮችን እንደወረደ በጥሬው ነው የሚረዱት፡፡ አስፐርገር መገለጫው ከሰው ሰው ስለሚለያይ መኖሩን በቀላሉ ለመለየት ያስቸግራል፡፡ህምናው በዋናነት ቶሎ መለየትና የማህበራዊ ክህሎት ስልጠና ነው፡፡ መልካም ጊዜ! ዶ/ር ዮናስ ላቀው
የሚያስከትለውን ነገር በእርግጠኝነት ስለማናውቅ! ነገሮች እየተለወጡ ባሉበት ፍጥነት ምን ሊፈጠር እንደሚችል በእርግጠኝነት መገመት አንችልም፡፡ መወሰን የምንችለው እንዴት እንደምንቀበለው ነው፡፡
አእምሮአችን ቅድሚያ የሚሰጠው ለደስታችን ሳይሆን ለደህንነታችን ነው፡፡ ስለወደፊቱ ሲያስብ በመጀመሪያ የሚያመዛዝነው ሊከሰት የሚችለውን አደጋ ወይም ችግር ነው፡፡ "የራሴን ስራ ጀምሬ ብከስርስ?" "አዲስ ኤሌክትሮኒክስ ገዝቼ ቢበላሽስ?" "አዲሱ ቦታ የሆነ ችግር ቢገጥመኝስ?" ...ወዘተ ይለናል፡፡ በእውነታው ግን ነገሮች እንደምንፈራው አይደሉም፡፡
ፍርሀት በአብዛኛው ከተሳሳተ አስተሳሰብ የሚመነጭ ስሜት ነው፡፡(በአብዛኛው!) ፍርሀት አስፈላጊ ነው፡፡ ነገር ግን እሱ ላይ ብቻ ካተኮርን ልናገኝ የምንችለውን ጥቅም፣ ለውጥ እንዳናይ ይጋርደናል፡፡የተለመደን ነገር መለየት ከባድ ነው፡፡ መለየት በችርቻሮም ቢሆን ሞት ነው፡፡ ነገር ግን ትዳር ውስጥ ስንገባ ላጤነትን መሰናበት አለብና፤ የግል ስራ ስንጀምር ደሞዝን ደህና ሰንብት ማለት አለብን...ወዘተ
ለፍርሀት መድሀኒቱ እቅድ ነው፡፡ በጣም የምንፈራው ነገር ቢደርስ ምን እናደርጋለን? ለዚህ መልስ ካዘጋጀን አዲሱ ነገር አስፈሪነቱ ይቀንሳል፡፡ ነገሮች እንዳሉ ቢቀጥሉ ጥቅም አለው፡፡ ደህንነት ይሰጠናል፡፡ ለደህንነቱ የምንከፍለው ዋጋ ግን እድገታችንን፣ ነፃነታችንን እምቅ ችሎታችን ነው፡፡
መልካም ጊዜ
Comments
Post a Comment