The big bang theory ላይ የተሳለው ገፀ ባህሪ ሼልደን ኩፐር ለአስፐርገር ሲንድረም ጥሩ ማሳያ ይሆናል፡፡ እናቱ ሁለቴ የአእምሮ ሀኪም ጋር ወስዳው ምንም የአእምሮ እክል የለብህም ቢባልም የሚያሳያቸው ፀባዮች አስፐርገር ሲንድረም እንዳለበት ይጠቁማሉ፡፡ አስፐርገር ሲንድረም ሰዎች አለምን የሚያዩበትን መንገድ እንዲሁም ከሰው ጋር የሚኖራቸውን ግንኙኘት የሚለውጥ ከኦቲዝም ህብር ህመሞች አንዱ ነው፡፡ እንደሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች የሌሎች ሰዎችን ስሜት ለመረዳት መቸገር፣ ለውጥ አለመፈለግ፣ ተመሳሳይ ነገሮችን ደጋግሞ መስራት ይታይባቸዋል፡፡ ከሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች በተሻለ የቋንቋ ክህሎታቸው እና አጠቃላይ የመገንዘብ /የመረዳት ችሎታቸው (ማህበራዊ ግንኙነትን ሳይጨምር) ጥሩ ነው፡፡ የተሻለ የመገንዘብና የንግግር ችሎታ ቢኖራቸውም ቋንቋን ሚረዱበት መንገድ የተለየ ነው፡፡ በተለይም ሽሙጥ፣ ስላቅን ለመረዳት ይቸገራሉ፡፡ ምሳሌያዊ አነጋገሮችን እንደወረደ በጥሬው ነው የሚረዱት፡፡ አስፐርገር መገለጫው ከሰው ሰው ስለሚለያይ መኖሩን በቀላሉ ለመለየት ያስቸግራል፡፡ህምናው በዋናነት ቶሎ መለየትና የማህበራዊ ክህሎት ስልጠና ነው፡፡ መልካም ጊዜ! ዶ/ር ዮናስ ላቀው
- ኦቲዝም ምንድነው?
- ከምንድነው የሚመጣው?
- ስርጭቱ ምን ይመስላል?
- ምልክቶቹ ምን ምን ናቸው?
- ቀድሞ ለመለየት ምን ማድረግ ይቻላል?
- ከኦቲዝም ጋር ተያይዞ ልዩ ተስእጦ ያላቸው ልጆችን እንዴት ማገዝ ይቻላል?
- አንድ ልጅ ኦቲዝም ሲኖረው ቤተሰብ ውስጥ ምን አይነት ተፅእኖ ያመጣል?
- ህክምና አለው ወይ?
- ህክምናው ምን ይመስላል?
- ከህክምናው ምን እንጠብቃለን?
- ከኦቲዝም ጋር የተያያዙ በብዛት የሚጠየቁ ጥያቄዎች ምንድናቸው?
ለእነዚህና ሌሎች ከኦቲዝም ጋር ለተያያዙ ጥያቄዎች ዶ/ር ዮናስ ባህረጥበብ (ተ/ፕሮፌሰር) የህፃናትና ታዳጊዎች የአእምሮ ህክምና ስፔሻሊስት በአንድ በኩል ዘመኑ ከደረሰበት ሣይንስና ምርምር፤ በሌላ በኩል ከብዙ አመታት ልምድ በመነሣት ኪናዊ በሆነ አቀራረብ በቅርቡ ያሣተሙት"ዓይኔን ተመልከተኝ" መፅሀፍ ምላሽ ይሰጣል፡፡
Comments
Post a Comment