The big bang theory ላይ የተሳለው ገፀ ባህሪ ሼልደን ኩፐር ለአስፐርገር ሲንድረም ጥሩ ማሳያ ይሆናል፡፡ እናቱ ሁለቴ የአእምሮ ሀኪም ጋር ወስዳው ምንም የአእምሮ እክል የለብህም ቢባልም የሚያሳያቸው ፀባዮች አስፐርገር ሲንድረም እንዳለበት ይጠቁማሉ፡፡ አስፐርገር ሲንድረም ሰዎች አለምን የሚያዩበትን መንገድ እንዲሁም ከሰው ጋር የሚኖራቸውን ግንኙኘት የሚለውጥ ከኦቲዝም ህብር ህመሞች አንዱ ነው፡፡ እንደሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች የሌሎች ሰዎችን ስሜት ለመረዳት መቸገር፣ ለውጥ አለመፈለግ፣ ተመሳሳይ ነገሮችን ደጋግሞ መስራት ይታይባቸዋል፡፡ ከሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች በተሻለ የቋንቋ ክህሎታቸው እና አጠቃላይ የመገንዘብ /የመረዳት ችሎታቸው (ማህበራዊ ግንኙነትን ሳይጨምር) ጥሩ ነው፡፡ የተሻለ የመገንዘብና የንግግር ችሎታ ቢኖራቸውም ቋንቋን ሚረዱበት መንገድ የተለየ ነው፡፡ በተለይም ሽሙጥ፣ ስላቅን ለመረዳት ይቸገራሉ፡፡ ምሳሌያዊ አነጋገሮችን እንደወረደ በጥሬው ነው የሚረዱት፡፡ አስፐርገር መገለጫው ከሰው ሰው ስለሚለያይ መኖሩን በቀላሉ ለመለየት ያስቸግራል፡፡ህምናው በዋናነት ቶሎ መለየትና የማህበራዊ ክህሎት ስልጠና ነው፡፡ መልካም ጊዜ! ዶ/ር ዮናስ ላቀው
የብዙ ሰዎች የኤሌክትሪክ ንዝረት ህክምና ግንዛቤ በትክክል ባልተሰሩ ፊልሞች ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ አማኑኤል ሆስፒታል በሳምንት ከ30 እስከ 50 ለሚደርሱ ሰዎች የኤሌክትሪክ ንዝረት ህክምና እንሰጣለን፡፡ የማይናገሩ የማይበሉ ታካሚዎችን ወደ ቀድሞ ማንነታቸው እንዲመለሱ ሲያደርግ ማየት ያስደስታል፡፡ የኤሌክትሪክ ንዝረት ህክምና በተለይ ለዲፕረሽን፣ ካታቶኒያ(የማይበሉ የማይናገሩ) ራስ የማጥፋት ሀሳብ ላላቸው እንዲሁም በንግግር ህክምና ወይም በመድሀኒት ለውጥ ላላሳዩ ውጤታማ የሆነ ህክምና ነው፡፡ የንዝረት ህክምና ከመሰጠቱ በፊት ታካሚው ወይም ቤተሰቡ በህክምናው ተስማምተው ፈቃዳቸውን ይሰጣሉ፡፡ ያለ ታካሚ ወይም ቤተሰብ ፈቃድ በጭራሽ አይሰጥም፡፡ ብዙ ፊልሞች ላይ የሚታየው የንዝረት ህክምና ከሰመመን መድሀኒቶች በፊት የነበረውን ነው፡፡ አማኑኤል የሚሰጠው የንዝረት ህክምና በአእምሮ ሀኪም፣ የሰመመን ባለሞያ እና ነርሶች ጥምረት ሲሆን ታካሚዎች ህመም እንዳይሰማቸውና ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን የሰመመን መድሀኒት ይሰጣቸዋል፡፡ ህክምናው በሚሰጥበት ጊዜም የልብ አመታታቸው አተነፋፈሳቸው በመከታታያ መሳሪያ(continuous monitoring) እንዲሁም በቧለሞያ ክትትል ይደረጋል፡፡ የንዝረቱ መጠን ከመድሀኒት አሰጣጥ ጋር ተመሳሳይ በሆነ መርህ ነው የሚመራው - በትንሹ ጀምሮ ቀስ ብሎ መጨመር፡፡ (Start low, go slow). በተጨማሪም አስተኛ የጎንዮሽ ጉዳት ያለው ውጤታማ መጠን፡፡ በአጠቃላይ ስለ ኤሌክትሪክ ንዝረት ህክምና ውጤታማነት በአለምአቀፍ ደረጃ ከሰማንያ አመታት፣ በሀገራቾን ደግሞ አስር አመታት በላይ የተደረጉት ውጤታማ ህክምናዎች ይመሰክራሉ፡፡ ፎቶው አማኑኤል ሆስፒታል የኤክትሪክ ንዝረት ህክምና ክፍል ...