The big bang theory ላይ የተሳለው ገፀ ባህሪ ሼልደን ኩፐር ለአስፐርገር ሲንድረም ጥሩ ማሳያ ይሆናል፡፡ እናቱ ሁለቴ የአእምሮ ሀኪም ጋር ወስዳው ምንም የአእምሮ እክል የለብህም ቢባልም የሚያሳያቸው ፀባዮች አስፐርገር ሲንድረም እንዳለበት ይጠቁማሉ፡፡ አስፐርገር ሲንድረም ሰዎች አለምን የሚያዩበትን መንገድ እንዲሁም ከሰው ጋር የሚኖራቸውን ግንኙኘት የሚለውጥ ከኦቲዝም ህብር ህመሞች አንዱ ነው፡፡ እንደሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች የሌሎች ሰዎችን ስሜት ለመረዳት መቸገር፣ ለውጥ አለመፈለግ፣ ተመሳሳይ ነገሮችን ደጋግሞ መስራት ይታይባቸዋል፡፡ ከሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች በተሻለ የቋንቋ ክህሎታቸው እና አጠቃላይ የመገንዘብ /የመረዳት ችሎታቸው (ማህበራዊ ግንኙነትን ሳይጨምር) ጥሩ ነው፡፡ የተሻለ የመገንዘብና የንግግር ችሎታ ቢኖራቸውም ቋንቋን ሚረዱበት መንገድ የተለየ ነው፡፡ በተለይም ሽሙጥ፣ ስላቅን ለመረዳት ይቸገራሉ፡፡ ምሳሌያዊ አነጋገሮችን እንደወረደ በጥሬው ነው የሚረዱት፡፡ አስፐርገር መገለጫው ከሰው ሰው ስለሚለያይ መኖሩን በቀላሉ ለመለየት ያስቸግራል፡፡ህምናው በዋናነት ቶሎ መለየትና የማህበራዊ ክህሎት ስልጠና ነው፡፡ መልካም ጊዜ! ዶ/ር ዮናስ ላቀው
የበላያችን በስራችን ላይ አሉታዊ ነገር ተናግሮን ይቅርና ፌስቡክ ላይ ፖስት ያደርግነው ሁለት ላይክ ብቻ ሲያገኝ ጥሩ ስሜት አይስማንም፡፡በስራችንም ሆነ በግል ህይወታችን ስኬታማ ለመሆን ትችትን መቋቋም ብሎም መቀበል ያስፈልጋል፡፡
ትችት ምንድነው?
ትችት ሰዎች ለሆነ ድርጊት ወይም ሁኔታ የሚሰጡት አስተያየት ሲሆን ጥሩ ወይም መጥፎ ሊሆን ይችላል ፡፡ ትችት ሁሉም ቦታ አለ፡፡ በስራቦታ፤በጓደኛ፤በቤተሰብ፤በፍቅረኛ፤ሊሆን ይችላል፡፡ሰዎች በተለያየ ምክንያት ትችት ሊሰነዝሩ ይችላሉ፡፡ቤተሠብ ጓደኛ በቀና አስተሳሰብ የተሠማቸውን ለመግለፅ ወይም እንድንሻሻል በማሠብ አለቆች ሠራተኞች የበለጠ እንደሰሩ ለማድረግ ሊሆን ይችላል፡፡በተቃራኒው ደግሞ በቅናት ፤በጥላቻ ስህተት ፈላጊ በመሆንና የተሻሉ እንዲሆኑ ለማሣየት ሊሆን ይችላል፡፡
ጥሩ ያልሆኑ ትችቶች ሰዎች ለራሣቸው የሚሰጡትን ግምት በመቀነስ የበታችነት ስሜት እንዲሰማቸው ያደርጋሉ፡፡ጥሩ ያልሆኑ ትችቶች መብሰልስል፤ጭንቀት፤ድብርት “ለምን እንደዚህ ተባልኩ?” እያሉ እንቅልፍ ማጣት ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡
ትችትን በመፍራት አቅም እያላቸው መስራት የሚያቆሙም አይጠፉም፡፡ትችት የማይቀር ነገር በመሆኑ ብዙ መጨነቅ አይገባንም፡፡የሚሰነዘሩብንን ትችቶች ለማቋቋም የሚረዱ የተወሰኑ ነጥቦች፤
-
ማዳመጥ ለትችት ምላሽ ከመስጠታችን በፊት ጠቃሚ ነው አይደለም የሚለውን መለየት አለብን፡፡ ጓደኛችን አብረን ከተዝናናን በኃላ ‘’ገንዘብ ታባክናህ’’ ቢለን ሊሠማን ይችላል፡፡ ነገር ግን ያመለከተው ነገር ራሣችንን እንድንለውጥ የሚያግዘን ይሆናል፡፡ምላሽ ለመስጠት ከመፍጠናችን በፊት ማዳመጥና ምን ለማለት እንደሆነ መረዳት ጥሩ ነው፡፡
- በተረጋጋ ሁኔታ መመለስ የተሰጠን ትችት ጠቃሚ ከሆነ በአክብሮት አመስግነን መቀበል፤አሉታዊ ከሆነም በአክብሮት ምላሽ መስጠት (አሉታዊ ሲሆን ቀላል ላይሆን ይችላል)፡፡
- በግል አለመውሰድ ሰዎች የሚሰጡት ትችት ስለኛ ከሚናገረው ይበልጥ ስለእነሱ እንደሚናገር ማወቅ አለብን፡፡በተጨማሪም አንድ ድርጊት ላይ ያለን ድክመት ስለማንነታችን እንደማይናር ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ሂሣብ ላይ ቀሽም ከሆንን የሚያሳየው ሂሳብ ላይ ቀሽም እንደሆንን እንጂ እኛ ቀሺም እንደሆንን አይደለም፡፡ አንዳንዴ ትችት ደካማ ጎን ላይ በማተኮር ራሣችንን እንድንጠራጠርና ያሉንን ብዙ ብቃቶች እንድንዘነጋ ያረገናል፡፡ ስለዚህ ትችትን በግል አለመውሰድ ለራሣችን ያለን ግምት እንዳይቀነስ ይረዳናል፡፡
- ጠንክሮ መቀጠል ጠቃሚ ትችትን ተቀብሎ መቀጠል ራሣችንን እንድናሻሽል ይረዳል፡፡አሉታዊ ትችት የአንድ ሰው አመለካከት ብቻ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል፡፡መድረስ ያሰብንበትን አላማ ላይ እንዳንደርስ አሉታዊ ትችቶች እንዲገድቡን መፍቀድ የለብንም ፡፡ትልልቅ ፈጠራ የሰሩ ሰዎች መጀመሪያ ሀሣባቸውን ሲናገሩ “ዋው የሚገርም ትልቅ ሀሣብ ነው” አልተባሉም፡፡ በተቃራኒው “ይህ የማይሆን ነገር ነው፡፡” እና “አትጃጃል ጊዜህን አታጥፋ፡፡” ነው የተባሉት፡፡
ለማጠቃለል ሼክስፒር እንዳለው የመስታወት ያህል ጥራት የበረዶ ያህል ንጣት ቢኖረንም ሰዎች ከሚስነዝሩብን ትችት አናመልጥም፡፡የሚያደርሰውን ተፅእኖ መቋቋም እንዲሁም ራሣችንን ለማሻሻል መጠቀም ግን ይቻላል፡፡
very very thank you
ReplyDelete