Skip to main content

Posts

Showing posts from March, 2018

Featured Post

አስፐርገር ሲንድረም (Asperger syndrome)

The big bang theory ላይ የተሳለው ገፀ ባህሪ ሼልደን ኩፐር ለአስፐርገር  ሲንድረም ጥሩ ማሳያ ይሆናል፡፡ እናቱ ሁለቴ የአእምሮ ሀኪም ጋር ወስዳው ምንም የአእምሮ እክል የለብህም ቢባልም የሚያሳያቸው ፀባዮች አስፐርገር ሲንድረም እንዳለበት ይጠቁማሉ፡፡ አስፐርገር ሲንድረም ሰዎች አለምን የሚያዩበትን መንገድ እንዲሁም ከሰው ጋር የሚኖራቸውን ግንኙኘት የሚለውጥ ከኦቲዝም ህብር ህመሞች አንዱ ነው፡፡ እንደሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች የሌሎች ሰዎችን ስሜት ለመረዳት መቸገር፣ ለውጥ አለመፈለግ፣ ተመሳሳይ ነገሮችን ደጋግሞ መስራት ይታይባቸዋል፡፡ ከሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች በተሻለ የቋንቋ ክህሎታቸው እና አጠቃላይ የመገንዘብ /የመረዳት ችሎታቸው (ማህበራዊ ግንኙነትን ሳይጨምር) ጥሩ ነው፡፡ የተሻለ የመገንዘብና የንግግር ችሎታ ቢኖራቸውም ቋንቋን ሚረዱበት መንገድ የተለየ ነው፡፡ በተለይም ሽሙጥ፣ ስላቅን ለመረዳት ይቸገራሉ፡፡ ምሳሌያዊ አነጋገሮችን እንደወረደ በጥሬው ነው የሚረዱት፡፡ አስፐርገር መገለጫው ከሰው ሰው ስለሚለያይ መኖሩን በቀላሉ ለመለየት ያስቸግራል፡፡ህምናው በዋናነት ቶሎ መለየትና የማህበራዊ ክህሎት ስልጠና ነው፡፡ መልካም ጊዜ! ዶ/ር ዮናስ ላቀው

አራቱ የልጅ አስተዳደግ አይነቶች (Parenting styles)

ልጆች የሚያድጉበት መንገድ ከፍ ሲሉ ከሰው ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት፣ የፍቅር ጓደኛ ምርጫ፣ ስኬት፣ በራስ መተማመን ላይ ትልቅ ሚና አለው፡፡ በተጨማሪም ከሴክስ፣ከገንዘብና ከአማች ቀጥሎ ትዳር ውስጥ አለመግባባት የሚፈጥረው የልጆች አስተዳደግ ነው፡፡ እንደ የስነ-ነልቦና ባለሞያዎች ወላጆች ልጆቻቸውን የሚያሳድጉባቸው መንገዶች በአራት ይከፈላሉ፡፡     አምባገነን (ኮስታራ) ፦ ይህ አይነት የልጅ አስተዳደግ በአለማችን በይበልጥ ደግሞ በሀገራችን ለረጅም ጊዜ የነበረ የማሳደጊያ መንገድ ነው፡፡ ከእናቶች ይልቅ ደግሞ አባቶች ላይ ይስተዋላል፡፡ እነዚህ ወላጆች ልጆቻቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው 'ኮስተር' ብለው ይነግሩና ልጆች 'ወለም ዘለም' ሳይሉ እንዲከተሉ ይጠብቃሉ፡፡ እንደዚህ የሚያድጉ ልጆች በአብዛኛው ስኬታማ ለመሆንና 'ትክክል' የሆኑ ነገሮችን ለማድረግ የሚጣጣሩ ሲሆኑ አዲስ ነገር ለመሞከር ወይም ያልተለመደ ስራ ለመስራት ይከብዳቸዋል፡፡ አንዳንዶቹ ከቤተሰብ ሲርቁ የማያምኑባቸውን ነገሮች ለማድረግ ይገፋፋሉ፡፡   የሚያሞላቅቁ (ሁሉንም የሚፈቀዱ)፦ ይሄ የልጅ አስተዳደግ በቅርብ የተጀመረ ሲሆን በከተማዎች በጣም እየተስፋፋ የመጣ አይነት ነው፡፡ እነዚህ ወላጆች ልጆቻቸው ያለ ገደብ እንደፈለጉ አንዲሆኑ ይፈቀዳሉ፡፡ ልጆቻቸው ያለ ከልካይና ያለ ገደብ እንደልባቸው እንዲሆኑ ከመፍቀድ ውጪ ምን ማድረግ እንዳለባቸው አይነግሯቸውም፡፡ ልጆቻቸው እስከፈለጉ ድረስ ከቤተሰቡ አቅም በላይ ቢሆንም እንኳ ለማሟላት ይጣጣራሉ፡፡እንደዚህ የሚያድጉ ልጆች ከቤት ውጭ እንደፈለጉ መሆን ስለማይችሉ ጭንቀት ይሰማቸዋል፡፡ የተወሰኑት ለምንም ነገር ሀላፊነት የማይሰማቸው ይሆናሉ፡፡   ግድ የለሽ፦ እነዚህ ወላ...

ለምን ትታው አትሄድም?

  አንድ ሴት በፍቅር ጓደኛዋ ወይም በባሏ ተደጋጋሚ ጥቃት ሲደርስባት "ለምን ትታው አትሄድም?" የሚል ጥያቄ ይፈጥራል፡፡ መልሱ ግን ለጠያቂ እንደሚቀለው አይደለም፡፡ ብዙ ጊዜ አስቸጋሪ ፀባይ ካለው ሰው ጋር የፍቅር ግንኙነት ያላቸው ሴቶች ትዳራቸው እንዳይፈርስ እና ፍቅራቸው እንዲቀጥል የሚለውን መቀበል፣ ፍላጎቱ አንዲሟላ መጣጣር እንዲሁም የሚያምኑባቸውን ነገሮች አስከመተው ይደርሳሉ፡፡ ግን ይሄም በቂ አይሆንም፡፡ ነገር ግን እንደዚህም ሆኖ ትተው ለመሄድ ይቸገራሉ፡፡ ምክንያቶቹ እነሆ፦   1. ተስፋ- ጥቃት የሚጀምረው ከተወሰነ ጊዜ በኃላ ነው፡፡ (ከመጀመሪያው እንደዚሁ ቢሆን ለውሳኔ ቀላል ይሆን ነበር፡፡) መጀመሪያ አካባቢ ተንከባካቢ፣ አክብሮት ያለው፣ ጥሩ አፍቃሪ ነበረ፡፡ከጊዜ በኋላ የመጣ ስለሆነ፤ ከጊዜ በኃላ እንደበፊቱ ጥሩ አፍቃሪ ይሆናል በሚል ተስፋ ያደርጋሉ ፡፡ በተጨማሪም የበፊቱ የፍቅር ጊዜያት ትዝታ ስላለ ጨክኖ ለመለያየት ይቸገራሉ፡፡   2. ፍርሀት- ጥቃት የሚያደርሱ ሰዎች ፍቅረኛቸው ልትለያቸው እንደሆነ ሲያውቁ የተለያዩ ማስፈራሪያ ይሰነዝራሉ፡፡ "ልጆቹን እወስዳቸዋለሁ!!" "ቤተሰቦችሽን እንደዚህ አደርጋለሁ!!" "ትተሽኝ የምትኖሪ ይመስልሻል" ...ወዘተ እያሉ ይዝታሉ፡፡አንዳንዶቹ ከዛቻም ያልፋሉ፡፡ እነዚሀ ነገሮች ትታው ብትሄድ ሊፈጠር የሚችለውን በመፍራት እንድትቆይ ያደርጓታል፡፡   3. ማህበራዊ ጫናና ስህተት እንደሆነ አለማወቅ- ጥቃት የሚያደርሱ ሰዎች ብዙ ጊዜ ሴቷን የተለያየ ሰበብ በመፍጠር ከቤተሰብ ከጓደኛ ይነጥሏታል፡፡ በተጨማሪ ብዙዎቹ ጥቃት የሚያደርሱ ሰዎች "የውጭ አልጋ የቤት ቀጋ" የሚባሉ አይ...

"የአማኑኤል መድሃኒት" እና ዝምተኛው ብዙሀን

የአእምሮ ህክምና ውጤቱ በአጠቃላይ ጥሩ ነው፡፡ ከሌሎች የህክምና ስፔሻሊቲዎች (የውስጥ ደዌ፣ የቀዶ ህክምና፣ የህፃናት ህክምና...ወዘተ) ጋር ተነፃፃሪ የሆነ ውጤት ያመጣል፡፡ ሁሉም የህክምና ስፔሻሊቲዎች እንደሚታከሙ ሰዎች የተወሰኑ ሰዎች ለውጥ ላያሳዩ እንዲሁም እጅግ በጣም ጥቂቶች ላይ ህመሙ ሊባባስ ይችላል፡፡ ከአእምሮ ህክምና ጥሩ ውጤቶች ይልቅ " የአማኑኤል መድሃኒት ከወሰደ በኋላ ህመሙ ባሰበት፡፡" ፣ "የአማኑኤል መድሀኒት ያጀዝባል፡፡" እና የመሣሠሉት አባባሎች ጎልተው ይሰማሉ፡፡ ለምን? ምክኒያቶቹን ከፋፍሎ ማየት ያስፈልጋል፡፡   1. የህመሙ አይነት፡- አብዛኛዎቹ የአእምሮ ህመሞች ( ዘጠና አምስት ከመቶ በላይ)ለአጭር ጊዜ የሚቆዩ ወይም በቀላሉ ሊታከሙ የሚችሉ ሲሆኑ በጣም ጥቂቶቹ የረዥም ጊዜ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ናቸው፡፡ ምልክቱ ሳል ቢሆን በአብዛኛው ጉንፋን ሊሆን እንደሚችል እና በጣም በጥቂቶች ቲቢ እንደሚሆነው ማለት ነው፡፡በአብዛኛው ታካሚዎች አማኑኤል ሆስፒታል የሚሄዱት ብዙ ነገሮች ከተሞከሩ በኋላ እንደመጨረሻ አማራጭ ነው፡፡ አንድ ሰው ሳይታከም ረጅም ጊዜ ከቆየ ከህክምና የሚገኘው ውጤት እንደሚጠበቀው አይሆንም፡፡   2.የህክምና ሁኔታ፦ አማኑኤል ሆስፒታል በሀገራችን ብቸኛው የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እንደመሆኑ ከፍተኛ የሆነ መጨናነቅ ይስተዋላል፡፡ በስራ ጫና ፣በሀኪሞች መቀያየር የህመሙን አይነትና መጠን አለመለየት፣ መድሃኒቶችን ከሚያስፈልገው ጊዜ እርዝመት ወይም መጠን በላይ መስጠት ያስከትላል፡፡ (የአእምሮ ህክምና ከአማኑኤል በተጨማሪ በጥቁር አንበሳ፣ ዘውዲቱ፣ የካቲት፣ ጳውሎስ እንዲሁም በግል የአእምሮ ህክምና ተቋማት ይሰጣል፡፡ )   3. ቅር የተሰኙ...

ኦቲዝም(Autism)

- ኦቲዝም ምንድነው? - ከምንድነው የሚመጣው? - ስርጭቱ ምን ይመስላል? - ምልክቶቹ ምን ምን ናቸው? - ቀድሞ ለመለየት ምን ማድረግ ይቻላል? - ከኦቲዝም ጋር ተያይዞ ልዩ ተስእጦ ያላቸው ልጆችን እንዴት ማገዝ ይቻላል? - አንድ ልጅ ኦቲዝም ሲኖረው ቤተሰብ ውስጥ ምን አይነት ተፅእኖ ያመጣል? - ህክምና አለው ወይ? - ህክምናው ምን ይመስላል? - ከህክምናው ምን እንጠብቃለን? - ከኦቲዝም ጋር የተያያዙ በብዛት የሚጠየቁ ጥያቄዎች ምንድናቸው?    ለእነዚህና ሌሎች ከኦቲዝም ጋር ለተያያዙ ጥያቄዎች ዶ/ር ዮናስ ባህረጥበብ (ተ/ፕሮፌሰር) የህፃናትና ታዳጊዎች የአእምሮ ህክምና ስፔሻሊስት በአንድ በኩል ዘመኑ ከደረሰበት ሣይንስና ምርምር፤ በሌላ በኩል ከብዙ አመታት ልምድ በመነሣት ኪናዊ በሆነ አቀራረብ በቅርቡ ያሣተሙት"ዓይኔን ተመልከተኝ" መፅሀፍ ምላሽ ይሰጣል፡፡