Skip to main content

Posts

Showing posts from April, 2018

Featured Post

አስፐርገር ሲንድረም (Asperger syndrome)

The big bang theory ላይ የተሳለው ገፀ ባህሪ ሼልደን ኩፐር ለአስፐርገር  ሲንድረም ጥሩ ማሳያ ይሆናል፡፡ እናቱ ሁለቴ የአእምሮ ሀኪም ጋር ወስዳው ምንም የአእምሮ እክል የለብህም ቢባልም የሚያሳያቸው ፀባዮች አስፐርገር ሲንድረም እንዳለበት ይጠቁማሉ፡፡ አስፐርገር ሲንድረም ሰዎች አለምን የሚያዩበትን መንገድ እንዲሁም ከሰው ጋር የሚኖራቸውን ግንኙኘት የሚለውጥ ከኦቲዝም ህብር ህመሞች አንዱ ነው፡፡ እንደሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች የሌሎች ሰዎችን ስሜት ለመረዳት መቸገር፣ ለውጥ አለመፈለግ፣ ተመሳሳይ ነገሮችን ደጋግሞ መስራት ይታይባቸዋል፡፡ ከሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች በተሻለ የቋንቋ ክህሎታቸው እና አጠቃላይ የመገንዘብ /የመረዳት ችሎታቸው (ማህበራዊ ግንኙነትን ሳይጨምር) ጥሩ ነው፡፡ የተሻለ የመገንዘብና የንግግር ችሎታ ቢኖራቸውም ቋንቋን ሚረዱበት መንገድ የተለየ ነው፡፡ በተለይም ሽሙጥ፣ ስላቅን ለመረዳት ይቸገራሉ፡፡ ምሳሌያዊ አነጋገሮችን እንደወረደ በጥሬው ነው የሚረዱት፡፡ አስፐርገር መገለጫው ከሰው ሰው ስለሚለያይ መኖሩን በቀላሉ ለመለየት ያስቸግራል፡፡ህምናው በዋናነት ቶሎ መለየትና የማህበራዊ ክህሎት ስልጠና ነው፡፡ መልካም ጊዜ! ዶ/ር ዮናስ ላቀው

ምቀኝነት

ምቀኝነት አንድ ሰው እንዲኖረው የሚፈልገውን ችሎታ፣ ስኬት፣ ንብረት...ወዘተ ሌላ ሰው ሲኖረው የሚፈጠር ስሜት ሲሆን መሰረታዊ ከሆኑት ስሜቶቾ አንጻር ሲታይ የንዴትና የሀዘን ድብልቅ ነው፡፡ ሌላ ሰው የተሻለ ነገር ሲሰራ ወይም ሲኖረው ሁለት አይነት ስሜት ሊፈጥር ይችላል፡፡ አድናቆት ወይም ምቀኝነት፡፡ አድናቆት የሌላውን መሻል በትህትና መቀበል ሲሆን፤ ምቀኝነት በንዴት ላለመቀበል መሞከር ነው፡፡ ማን ማንን ይመቀኛል? ሰዎች የሚመቀኙት ከእነሱ ጋር ተቀራራቢ ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎችን ነው፡፡ ጓደኛ፣ ጎረቤት፣ የስራ ባልደረባ ...ወዘተ፡፡ ጫማህን የሚጠርገው ሊስትሮ አንተ የተሻለ ኑሮ ስራ ስላለህ ምቀኝነት አይሰማውም፡፡ ይልቁንም አጠገቡ ያለ ሌላ ሊስትሮ የተሻለ ገንዘብ ሲያገኝ ነው ምቀኝነት የሚሰማው፡፡ ጎረቤትህ የተሻለ ቤት ስትሰራ ምቀኝነት ይሰማው ይሆናል እንጂ አላሙዲን አዲስ ህንፃ ቢሰራ ምንም ስሜት አይፈጥርበትም፡፡ በአጠቃላይ ምቀኛ ከሩቅ አይመጣም፡፡   ምቀኝነት ወይስ ቅናት? አንዳንድ ሰዎች ሁለቱን ሲያቀያይሩ ይስተዋላል፡፡ ነገር ግን የተለያዩ ስሜቶች ናቸው፡፡ ቅናት ቦታ የምንሰጠው ነገር እንዳይወሰድብን ስንፈራ የሚፈጠር ስሜት ሲሆን እንዳይወሰድ የምንፈልገውን ነገር ለመጠበቅ ጥረት እንድናደርግ የሚገፋፋ ነው፡፡ በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ሲፈጠር ሰዎች ረጅም (አንዳንድ ጊዜ ከልክ ያለፈ) ርቀት እንዲሄዱ ያደርጋል፡፡ ምቀኝነት የሚፈጠረው አንድ ሰው ቢኖረው የሚመኘውን (ነገር ግን የሌለውን) ሌላ ሰው ሲኖረው የሚፈጠር ሲሆን ልዩነቱን ለማጥበብ ሌላውን ካለበት ለማውረድ ወይም ራስን ከፍ ለማድረግ እንዲጣጣር ይገፋፋል፡፡ "አላውቃትም እንዴ እንዴት እንደነበረች..." "እኔ ገንዘብ ሰጥቼው አይደል ስራ የጀመረ...

በዓልን ከአማች ጋር ማሳለፍ

በዓል ሲመጣ ባለትዳሮች ላይ "ማን ጋር ነው የምንሄደው?" የሚል ጥያቄ ይፈጠራል፡፡ በተጨማሪም ብዙ ሰዎች በዓልን ከአማች ጋር ማሳለፍ ያሳስባቸዋል፡፡ ማሳሰቡ ወደ ጫና እንዳይለወጥ የሚያግዙ አና አለፍ ሲልም ጥሩ ጊዜ ለማሳለፍ የሚረዱ አምስት ነጥቦች፦   1. በግልፅ መነጋገር ቀደም ብሎ የትኛውን በዓል ማን ጋር እንደሚያሳልፉ መነጋገር ጊዜው ሲደርስ የሚፈጠረውን አለመግባባት ያስቀራል፡፡ የትዳር የመጀመሪያዎቹን በዓላት አከባበር የወደፊቱን ልማድ ስለሚወስኑ በጊዜ ተነጋግሮ መወሰኑ የተለያየ ግምት እንዳይኖር ያደርጋል፡፡   2. ቅድሚያ ለትዳር አጋር መስጠት ለባላቸው/ለሚስታቸው ቅድሚያ የሚሰጡ ጥሩ ትዳር ይኖራቸዋል፡፡ ቤተሰቦቻቸውን የሚወዱና የሚያከብሩ ሲሆኑ ለትዳራቸው ግን ከሁሉም በላይ እንደሆነ ያስታውሳሉ፡፡ አንዳንድ ቤተሰቦች ውስጥ የሰው ትዳር ላይ ጣልቃ የሚገባና አስተያየት የሚሰጥ ሰው ይኖራል፡፡ ባልና ሚስት አንድ እንደሆኑ በማሳየት ክፍተት እንዳይፈጠር ማድረግ ይችላሉ፡፡   3. መቼ እንደምትመለሱ በቅድሚያ መወሰን አማች ጋር ከመሄድ በፊት ምን ያህል እንደምትቆዩ ለምን መመለስ እንደለባችሁ መነጋገር፡፡ መሄድ ሲኖርባችሁ ተመሳሳይ መልስ መስጠት ያስችላል፡፡ ሌላ ሀገር የምትሄዱ ከሆነ የምታርፉበትን ቦታ በቅድሚያ ማዘጋጀት ጥሩ ነው፡፡( ከአማች ጋር ቢጃማ ለብሰው መገናኘት የማይመቻቸው ሆቴል ቀደም ብለው እንዲይዙ ይመከራል፡፡)   4. አንድ ቀን መሆኑን ማስታወስ ምንም ይሁን ምን አንድ ቀን መታገስ አይከብድም፡፡ ከተወሰኑ ሰዓታት በኋላ አንደምትመለሱ ማሰብ የተወሰነ መረጋጋት ይፈጥራል፡፡ አማቾች እንዲወዱን መፈለግ ተፈጥሯዊ ነው፡፡ ነገር ግን ...

አዎንታዊ ስነ ልቦና (Positive Psychology)

የአእምሮ ህመምን ማከም እንደሚያስፈልገው ሁሉ የአእምሮ ጤናን ማጎልበት፣ የሰዎች ድክመት ላይ ከማተኮር ጥንካሬያቸው ላይ ማተኮር፣ ጥሩ ያልሆኑትን ለማቅናት የሚሞክረውን ያህል ምርጥ የሆኑትን አንዲያድጉ ማገዝ የአዎንታዊ ስነልቦና ትኩረቶች ናቸው፡፡ የሰው ልጆችን ኑሮ በተሟላ እና በተመጣጠነ መልኩ ለመረዳት ይሞክራል፡፡ "ሰዎች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች እንዴት መፍታት ይችላሉ?" ከሚለው መደበኛው የስነ ልቦና ሀሳብ በተቃራኒው የቆመ አይደለም፡፡ በአንጻሩ የተለመደውን ስነ ልቦና የሚያግዝና አድማሱን የሚያሰፋ ነው፡፡ ሰዎች ከውልደት እስከ ሞት የሚያልፉባቸውን ሂደቶች ያጠናል፡፡ ሰዎች መሆን የሚችሉትን 'ምርጡን እራሳቸውን' እንዲሆኑ እንዲሁም የሚያደርጓቸውን ነገሮች በተሻለ መንገድ ማድረግ እንዲችሉ ያግዛል፡፡ በህይወት ውስጥ ጥሩ ነገሮች እንዳሉ ሁሉ በዛው ልክ መጥፎ ነገሮችም አሉ፡፡ የአዎንታዊ ስነ ልቦና ዋነኛ እሳቤው 'ጥሩ ህይወት' ውጣ ውረድን ከማለፍና ችግሮችን ከመቋቋም ከፍ ያለ መሆን አለበት የሚል ነው፡፡ ሰዎች በራሳቸው መንገድ ደስተኛ የሚያደርጋቸውንና በህይወታቸው የሚሰማቸውን እርካታ የሚወስኑ ነገሮችን ሲጠየቁ የሚሰጧቸው ምላሾች በሚያስገርም ሁኔታ ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ ከአሜሪካ ሚሊየነሮች እስከ የህንድ ጎዳና ተዳዳሪዎች የሰጧቸው ምላሾች ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቀጥለው የተዘረዘሩት ዘር ፣ ፆታ፣ የትምህርት ደረጃ ሳይለዩ ከደስታና ከአእምሮ ጤንነት ጋር ከፍተኛ ተያያዥነት አላቸው፡፡   ** የጓደኞች መኖር   ** ትዳር   ** ተጫዋች መሆን   ** አመስጋኝ መሆን   ** ሀይማኖተኛ ሰው መሆን   ** መዝና...