The big bang theory ላይ የተሳለው ገፀ ባህሪ ሼልደን ኩፐር ለአስፐርገር ሲንድረም ጥሩ ማሳያ ይሆናል፡፡ እናቱ ሁለቴ የአእምሮ ሀኪም ጋር ወስዳው ምንም የአእምሮ እክል የለብህም ቢባልም የሚያሳያቸው ፀባዮች አስፐርገር ሲንድረም እንዳለበት ይጠቁማሉ፡፡ አስፐርገር ሲንድረም ሰዎች አለምን የሚያዩበትን መንገድ እንዲሁም ከሰው ጋር የሚኖራቸውን ግንኙኘት የሚለውጥ ከኦቲዝም ህብር ህመሞች አንዱ ነው፡፡ እንደሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች የሌሎች ሰዎችን ስሜት ለመረዳት መቸገር፣ ለውጥ አለመፈለግ፣ ተመሳሳይ ነገሮችን ደጋግሞ መስራት ይታይባቸዋል፡፡ ከሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች በተሻለ የቋንቋ ክህሎታቸው እና አጠቃላይ የመገንዘብ /የመረዳት ችሎታቸው (ማህበራዊ ግንኙነትን ሳይጨምር) ጥሩ ነው፡፡ የተሻለ የመገንዘብና የንግግር ችሎታ ቢኖራቸውም ቋንቋን ሚረዱበት መንገድ የተለየ ነው፡፡ በተለይም ሽሙጥ፣ ስላቅን ለመረዳት ይቸገራሉ፡፡ ምሳሌያዊ አነጋገሮችን እንደወረደ በጥሬው ነው የሚረዱት፡፡ አስፐርገር መገለጫው ከሰው ሰው ስለሚለያይ መኖሩን በቀላሉ ለመለየት ያስቸግራል፡፡ህምናው በዋናነት ቶሎ መለየትና የማህበራዊ ክህሎት ስልጠና ነው፡፡ መልካም ጊዜ! ዶ/ር ዮናስ ላቀው
የህክምና እገዛ የሚያስፈልግበት አንድ ሰዉ 60 ዓመት ይኖራል ቢባል በአማካይ 20ዓመታትን የሚያሳልፈዉ በእንቅልፍ ነዉ፡፡ ጥሩ እንቅልፍ ፦ በቀላሉ መተኛት መቻል፣ ያልተቆራረጠ እንቅልፍ እና ቀኑን ንቁ ሆኖ መዋልን ያጠቃልላል፡፡ ለሊት ላይ ጥሩ እንቅልፍ አለመተኛት ቀን መነጫነጭ፣ ትኩረት አለማድረግ፣የማስታወስ ችግር፣ ድብርትና ጭንቀት ያስተትላል፡፡ በሌላ መልኩ ሀሳቦቻችን፣ ስሜቶቻችንና በአጠቃላይ የአእምሮ ጤንነታችን የእንቅልፍ ስርአታችንን ሊያዛባዉ ይችላል፡፡ አንዳንዶቹ ምክንያቶች ተፈጥሮአዊና ለአጭር ጊዜ የሚቆዩ ለምሳሌ ፈተና ፣ ከፍቅር ጓደኛ ጋር አለመግባባት፣ የምንወደዉ ሰዉ በሞት ሲለየን የሚከሰቱ ሲሆኑ፤ሌሎች የእንቅልፍ ችግሮች ለረጅም ጊዜ የሚቆዩና የህክምና እገዛ የሚያስፈልጋቸዉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ጥሩ እንቅልፍ ለመተኛት በራሳችን ልናደርግባቸዉ የምንችላቸዉ ማድረግ የሚገባ - ቋሚ የመተኛ ሰዓት መመደብ - ቋሚ የመነሻ ሰዓት መመደብ (አእምሮአችን መደበኛ የሆነ የእንቅልፍ ፕሮግራም እንዲይዝ ያደርጋሉ ፡፡) - የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ (ጠዋት ጠዋት ቢሆን ይመረጣል ) - እራት በጊዜ መመገብ ( ከመተኛት ሶስት-አራት ሰዓት ቀደም ብሎ ) - መኝታ ክፍልን ብርሀን ያልበዛበት፣ ጸጥተኛና ቀዝቀዝ ያለ ማድረግ ማድረግ የሌለብን - አልጋ ላይ ሆኖ ስልክ ማወራት፤ ቻት ማደረግ - አልጋ ላይ ሆኖ ቲቪ ማየት፣ ሬዲዮ ማዳመጥ - አነቃቂ ነገሮች አመሻሽ ላይ መጠቀም - አልኮል መዉሰድ (ለአጭር ጊዜ የሚረዳ ቢመስልም ከጊዜ በኃላ የተቆራረጠ እንቅልፍ ያስከትላል ፡፡) ከላይ የተዘረዘሩት ቀላል ዘዴዎች ስለሆኑ የማይሰሩ ሊመስሉ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ብዙ የእንቅልፍ ችግር ያለባቸዉን ሰዎች ያለ መድኃኒት ጥ...