Skip to main content

Featured Post

አስፐርገር ሲንድረም (Asperger syndrome)

The big bang theory ላይ የተሳለው ገፀ ባህሪ ሼልደን ኩፐር ለአስፐርገር  ሲንድረም ጥሩ ማሳያ ይሆናል፡፡ እናቱ ሁለቴ የአእምሮ ሀኪም ጋር ወስዳው ምንም የአእምሮ እክል የለብህም ቢባልም የሚያሳያቸው ፀባዮች አስፐርገር ሲንድረም እንዳለበት ይጠቁማሉ፡፡ አስፐርገር ሲንድረም ሰዎች አለምን የሚያዩበትን መንገድ እንዲሁም ከሰው ጋር የሚኖራቸውን ግንኙኘት የሚለውጥ ከኦቲዝም ህብር ህመሞች አንዱ ነው፡፡ እንደሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች የሌሎች ሰዎችን ስሜት ለመረዳት መቸገር፣ ለውጥ አለመፈለግ፣ ተመሳሳይ ነገሮችን ደጋግሞ መስራት ይታይባቸዋል፡፡ ከሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች በተሻለ የቋንቋ ክህሎታቸው እና አጠቃላይ የመገንዘብ /የመረዳት ችሎታቸው (ማህበራዊ ግንኙነትን ሳይጨምር) ጥሩ ነው፡፡ የተሻለ የመገንዘብና የንግግር ችሎታ ቢኖራቸውም ቋንቋን ሚረዱበት መንገድ የተለየ ነው፡፡ በተለይም ሽሙጥ፣ ስላቅን ለመረዳት ይቸገራሉ፡፡ ምሳሌያዊ አነጋገሮችን እንደወረደ በጥሬው ነው የሚረዱት፡፡ አስፐርገር መገለጫው ከሰው ሰው ስለሚለያይ መኖሩን በቀላሉ ለመለየት ያስቸግራል፡፡ህምናው በዋናነት ቶሎ መለየትና የማህበራዊ ክህሎት ስልጠና ነው፡፡ መልካም ጊዜ! ዶ/ር ዮናስ ላቀው

አዲስ ነገር ስንማር የምናልፍባቸው አራቱ ደረጃዎች

መኪና መንዳት ስንለማመድ ይሁን አዲስ ቋንቋ ስንማር አዲስ አፕሊኬሽን ስንጠቀም ይሁን አዲስ ስራ ስንጀመር በተመሳሳይ የምናልፍባቸው አራት ደረጃዎች አሉ፡፡


  1. አለማወቅን አለማወቅ፦ በዚህ ደረጃ ላይ ስንሆን ስለነገሩ ግንዛቤ ስለሌለን አለማወቃችንን እንኳ ልናውቅ አንችልም፡፡ ብስክሌት አይቶ የማያውቅ ልጅ ብስክሌት መንዳት እንደማይችል እንደማያውቀው ማለት ነው፡፡ እዚህ ደረጃ ላይ የሚኖረው ስሜት የአላዋቂ ደስታ ነው፡፡
  2. አለማወቅን ማወቅ፦ በፊት ከማናቀው ነገር ጋር ከተዋወቅን በኃላ የመጀመሪያዎቹ ሙከራዎች ስኬታማ አይሆኑም፡፡ (በምሳሌ እንደምትጠቀሰው ከበሮ) አለመቻልን መገንዘብ የሚፈጥረው ጭንቀት አለ፡፡ ይህንን ጭንቀት መቋቋም የማይችሉ አዲስነገር መማር፣መልመድ ወይም ማወቅ እዚህ ጋር ያቆማሉ፡፡
  3. ማወቅን ማወቅ፦ ልክ ብስክሌት መንዳት ስንለምድ ስለፔዳል እያሰብን እንደምንነዳው ወይም አዲስ ሀላፊ ስንሆን መመሪያ አገላብጠን እንደምንወስነው ማለት ነው፡፡ በዚህ ደረጃ ላይ አዲስ ነገር በመቻል ምክኒያት የሚመጣ ደስታ 'ምናልባት' ከሚል ፍርሀት ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ ይመጣል፡፡
  4. ማወቅን አለማወቅ፦ በዚህ ደረጃ ላይ ሲደረስ አዲሱ ነገር ከተፈጥሮአችን ጋር ስለሚዋሀድ እናደረገዋለን እንጂ አናስበው፡፡ ልክ አንድን ቋንቋ በደንብ ስንችል ቃላት ሳንመርጥ ስለ ሰዋሰው ሳንጨነቅ እንደምንናገው ማለት ነው፡፡ በዚህ ደረጃ ብስክሌት የሚነዳ ለምሳሌ የሚሄድበት ቦታ ሲደርስ ምን እንደሚያደርግ እንጂ ስለመሪ እና ፔዳል አያስብም፡፡
አምስተኛው ደረጃ የሚሆነው ሌላ አዲስ ነገር ለመማር፣ ለመልመድ እና ለማወቅ ከላይ የተጠቀሱትን እንደገና መጀመር ነው፡፡
 
መልካም ጊዜ!

Comments

Popular posts from this blog

አራቱ የልጅ አስተዳደግ አይነቶች (Parenting styles)

ልጆች የሚያድጉበት መንገድ ከፍ ሲሉ ከሰው ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት፣ የፍቅር ጓደኛ ምርጫ፣ ስኬት፣ በራስ መተማመን ላይ ትልቅ ሚና አለው፡፡ በተጨማሪም ከሴክስ፣ከገንዘብና ከአማች ቀጥሎ ትዳር ውስጥ አለመግባባት የሚፈጥረው የልጆች አስተዳደግ ነው፡፡ እንደ የስነ-ነልቦና ባለሞያዎች ወላጆች ልጆቻቸውን የሚያሳድጉባቸው መንገዶች በአራት ይከፈላሉ፡፡     አምባገነን (ኮስታራ) ፦ ይህ አይነት የልጅ አስተዳደግ በአለማችን በይበልጥ ደግሞ በሀገራችን ለረጅም ጊዜ የነበረ የማሳደጊያ መንገድ ነው፡፡ ከእናቶች ይልቅ ደግሞ አባቶች ላይ ይስተዋላል፡፡ እነዚህ ወላጆች ልጆቻቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው 'ኮስተር' ብለው ይነግሩና ልጆች 'ወለም ዘለም' ሳይሉ እንዲከተሉ ይጠብቃሉ፡፡ እንደዚህ የሚያድጉ ልጆች በአብዛኛው ስኬታማ ለመሆንና 'ትክክል' የሆኑ ነገሮችን ለማድረግ የሚጣጣሩ ሲሆኑ አዲስ ነገር ለመሞከር ወይም ያልተለመደ ስራ ለመስራት ይከብዳቸዋል፡፡ አንዳንዶቹ ከቤተሰብ ሲርቁ የማያምኑባቸውን ነገሮች ለማድረግ ይገፋፋሉ፡፡   የሚያሞላቅቁ (ሁሉንም የሚፈቀዱ)፦ ይሄ የልጅ አስተዳደግ በቅርብ የተጀመረ ሲሆን በከተማዎች በጣም እየተስፋፋ የመጣ አይነት ነው፡፡ እነዚህ ወላጆች ልጆቻቸው ያለ ገደብ እንደፈለጉ አንዲሆኑ ይፈቀዳሉ፡፡ ልጆቻቸው ያለ ከልካይና ያለ ገደብ እንደልባቸው እንዲሆኑ ከመፍቀድ ውጪ ምን ማድረግ እንዳለባቸው አይነግሯቸውም፡፡ ልጆቻቸው እስከፈለጉ ድረስ ከቤተሰቡ አቅም በላይ ቢሆንም እንኳ ለማሟላት ይጣጣራሉ፡፡እንደዚህ የሚያድጉ ልጆች ከቤት ውጭ እንደፈለጉ መሆን ስለማይችሉ ጭንቀት ይሰማቸዋል፡፡ የተወሰኑት ለምንም ነገር ሀላፊነት የማይሰማቸው ይሆናሉ፡፡   ግድ የለሽ፦ እነዚህ ወላ...

ሁለት ውብ ታሪኮች ከአማኑኤል ሆስፒታል

አማኑኤል ሆስፒታል የሰው ድክመት፣ ውድቀት፣ ህመም ብቻ የሚሰማበት የሚመስላቸው ሰዎች አይጠፉም፡፡ ነገር ግን በየቀኑ የመነሳት፣ የጥንካሬ፣የፅናትና የፍቅር ውብ ታሪኮች ይስተናገዳሉ፡፡ ሁለቱ በዚህ ሳምንት ከገጠመኝ እነሆ፦   1) አማኑኤል የሴቶች ዋርድ የሀኪሞች ክፍል ተቀምጬ ካርድ ላይ እየፃፍኩ ነው፡፡ በሩ ገርበብ ብሏል፡፡ አንድ ታካሚ ከአልጋዋ ከነጋ አልተነሳችም፡፡ የደበራት ትመስላለች፡፡ ገርበብ ባለው በር ትታየኛለች፡፡ አንድ ወጣት ሴት ፍራፍሬ በፌስታል ይዛ ልትጠይቃት ትገባለች። አይኗ ብርት ብሎ ከአልጋዋ ወዲያው ተነሳች። ተቃቀፉ፡፡ በቀናት ውስጥ ያላየንባት ደስታ ውስጥ ሆና መጫወት ጀመሩ፡፡ ጠያቂዎን አውቃታለሁ፡፡ ከሳምንት በፊት እዚሁ ሆስፒታል እዚሁ ክፍል ተኝታ ነበር፡፡ ጓደኛዋን ልትጠይቅ መምጣቷ ነው፡፡ ተኝታ የምትታከመው ድንገት አቀረቀረች፡፡ አይኗን ሳታነሳ ጓደኛዋን "ግን የምንድን ይመስልሻል?" ብላ ጠየቀቻት፡፡ ጓደኛዋ እቅፍ አደረገቻት "እሱ የፈጣሪ ስራ ነው፡፡ እኛ ግን መድሀኒታችንን እንወስዳለን አለቻት፡፡"... አንድ የኩላሊት ጠጠር ቀዶጥገና ሀኪም "ሀኪሙ ጠጠሩን ያወጣል፤ የሚያድነው ግን አምላክ ነው፡፡" ያለው ትውስ አለኝ፡፡   2) ታካሚ ወንድሙን ይዞ ኦፒዲ ይገባል፡፡ መልካቸው በጣም ይለያያል፡፡ "እባካችሁ ተኝቶ ይታከም?" አለን፡፡ "ያልተለመደ ፀባይ ሲታይበት አከራዮቻችን ቤት እንድንለቅ ጠየቁን፡፡ ለትንሽ ጊዜ ቢተኛ?" አለን፡፡ "ቤተሰቦቻችሁ የት ናቸው?" ብዬ ጠየቅኩት፡፡ መልሱ ያልጠበቅኩት ነበር፡፡ "ከተለያየ ቤተሰብ ነው የመጣነው ግን ወንድሜ ነው፡፡ በማደጎ አብረን ነው ያደግ...

አዎንታዊ ስነ ልቦና (Positive Psychology)

የአእምሮ ህመምን ማከም እንደሚያስፈልገው ሁሉ የአእምሮ ጤናን ማጎልበት፣ የሰዎች ድክመት ላይ ከማተኮር ጥንካሬያቸው ላይ ማተኮር፣ ጥሩ ያልሆኑትን ለማቅናት የሚሞክረውን ያህል ምርጥ የሆኑትን አንዲያድጉ ማገዝ የአዎንታዊ ስነልቦና ትኩረቶች ናቸው፡፡ የሰው ልጆችን ኑሮ በተሟላ እና በተመጣጠነ መልኩ ለመረዳት ይሞክራል፡፡ "ሰዎች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች እንዴት መፍታት ይችላሉ?" ከሚለው መደበኛው የስነ ልቦና ሀሳብ በተቃራኒው የቆመ አይደለም፡፡ በአንጻሩ የተለመደውን ስነ ልቦና የሚያግዝና አድማሱን የሚያሰፋ ነው፡፡ ሰዎች ከውልደት እስከ ሞት የሚያልፉባቸውን ሂደቶች ያጠናል፡፡ ሰዎች መሆን የሚችሉትን 'ምርጡን እራሳቸውን' እንዲሆኑ እንዲሁም የሚያደርጓቸውን ነገሮች በተሻለ መንገድ ማድረግ እንዲችሉ ያግዛል፡፡ በህይወት ውስጥ ጥሩ ነገሮች እንዳሉ ሁሉ በዛው ልክ መጥፎ ነገሮችም አሉ፡፡ የአዎንታዊ ስነ ልቦና ዋነኛ እሳቤው 'ጥሩ ህይወት' ውጣ ውረድን ከማለፍና ችግሮችን ከመቋቋም ከፍ ያለ መሆን አለበት የሚል ነው፡፡ ሰዎች በራሳቸው መንገድ ደስተኛ የሚያደርጋቸውንና በህይወታቸው የሚሰማቸውን እርካታ የሚወስኑ ነገሮችን ሲጠየቁ የሚሰጧቸው ምላሾች በሚያስገርም ሁኔታ ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ ከአሜሪካ ሚሊየነሮች እስከ የህንድ ጎዳና ተዳዳሪዎች የሰጧቸው ምላሾች ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቀጥለው የተዘረዘሩት ዘር ፣ ፆታ፣ የትምህርት ደረጃ ሳይለዩ ከደስታና ከአእምሮ ጤንነት ጋር ከፍተኛ ተያያዥነት አላቸው፡፡   ** የጓደኞች መኖር   ** ትዳር   ** ተጫዋች መሆን   ** አመስጋኝ መሆን   ** ሀይማኖተኛ ሰው መሆን   ** መዝና...

አምስቱ የፍቅር ቋንቋዎች

ሁለት ሰዎች የፈለገ ቢዋደዱ የፍቅር ግንኙነታቸው እንዲዘልቅ ትልቅ ጥረት ይጠይቃል፡፡ በዚህ ጥረት ውስጥ የፍቅር ቋንቋ ጉልህ ድርሻ ይይዛል፡፡ የፍቅር ተጣማሪ የሚጠብቀውንና የሚፈልገውን መረዳት የፍቅር ህይወትን ከማሻሻሉ ጋር ተያይዞ በአጠቃላይ ጥሩ ስሜት፣ ደስታና በስራ ላይ ውጤታማነት ያመጣል፡፡ ሰዎች ፍቅራቸውን የሚገልፁባቸው ወይም የተጣማሪያቸውን ድርጊት የሚረዱባቸው የተለያዩ መንገዶች አሉ፡፡ ጠቅለል ተደርገው በአምስት ሊመደቡ ይችላሉ፡፡ እነሆ፦ የፍቅር ቃላት የፍቅር ቃላት ለሚመርጡ ሰዎች ‹‹እወድሃለሁ›› ወይም ‹‹እወድሻለሁ›› የሚሉት ቃላት ትልቅ ትርጉም አላቸው፡፡ በተጨማሪም ከተጣማሪያቸው ለሚሰነዘር አድናቆት ትልቅ ቦታ ይሰጣሉ፡፡ቃላት የከበረ ዋጋ አላቸው፡፡ በተቃራኒው አሉታዊ ወይንም ስድብ የሚመስል ቃላት ይጎዳቸዋል፡፡ በቀላሉ ይቅር ለማለት ይቸገራሉ፡፡ ጥሩ ጊዜ   ይህ የፍቅር ቋንቋ ለተጣማሪ ያልተከፋፈለ ትኩረት ስለመስጠት ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ከቃላት ይልቅ የተጣማሪያቸውን ጊዜና ያልተከፋፈለ ትኩረት ማግኘት ጥሩ ስሜት ይፈጥርላቸዋል፡፡ በተቃራኒው የተከፋፈለ ትኩረት ፣ቀጠሮ መሰረዝና አለመደመጥ ያስከፋቸዋል፡፡ ስጦታ መቀበል   ለአንዳንድ ሰዎች የመወደድ ስሜት እንዲሰማቸው ስጦታዎች ያስፈልጋሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ቁሳዊያን ናቸው ማለት አይደለም፡፡ ከስጦታው ይበልጥ ስጦታን ለመስጠት የተደረገው ሀሳብ በስጦታ ሰጪው ያላቸውን ቦታ ያረጋግጥላቸዋል፡፡ ተግባራዊ እገዛ   ለእነዚህ ሰዎች ድርጊቶች ከቃላት ይበልጥባቸዋል፡፡ ተጣማሪያቸው እየለፉ ያለበትን አስቸጋሪ ጉዞ ተረድተው በተግባር ቢያግዟቸው ይመርጣሉ፡፡ ለእነሱ ተግባራዊ እገዛ የማሰብና የፍቅር መገለጫ ነው፡፡ ይህንን ቋንቋ...

ንዴትን እንዴት መቆጣጠር ይቻላል?

ተናዶ የማያውቅ ሰው አሳዩኝ እና አምጣ የወለደች በቅሎ አሳያችኀለሁ፡፡ ሁላችንም የሆነ አጋጣሚ ላይ እንናደዳለን፡፡ ልዩነቱ ንዴትን የምንቆጣጠርበት መጠን ነው፡፡ ተናደን የምንወስናቸው ውሳኔዎች ጊዜ ሲያልፍ ዋጋ ያስከፍላሉ፡፡ ዋጋው፦ ጊዜ ማባከን፣ እንቅልፍ ማጣት፣ ከሚወዱት ሰው መቆራረጥ፣ መታሰር...ወዘተ ሊሆን ይችላል፡፡ ንዴትን ለመቆጣጠር የሚረዱ የተወሰኑ ነጥቦች እነሆ፦ 1. መናደዳችንን መቀበል- እንዳልተናደድን ለማስመሰል መሞከር ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ የሚያናድደንን ሁኔታ እንዴት እንደምንለውጥ እንዳናስብ ከማድረግ አልፎ ለአእምሮ ጤንነታችን፣ ለጨጓራችን እንዲሁም ለደም ግፊታችን ጥሩ አይደለም፡፡ መናደዳችንን ስንቀበል ራሳችንን ማረጋጋት እንችላለን፡፡ ( "የማናውቀውንና የማንቀበለውን ችግር መለወጥ አንችልም፡፡" የሚለው አባባል በግልባጩም ትክክል ነው፡፡) 2. ዘርዝሮ መመልከት- መናደዳችንን ከተቀበልን በኃላ ለምን እንደተናደድን ማሰብ ያስፈልጋል፡፡ ቢቻል የተፈጠረውን ነገር ብንፅፈው የበለጠ ግልፅ ይሆናል፡፡ መፍትሄውም እንደዚያው፡፡ ስንዘረዝረው አንዳንዶቹን ችላ ብለን ማለፍ ያለብን ሌሎቹ ደግሞ ከመርሀችን ጋር ስለሚጋጩ ለመለወጥ የሆነ ነገር ማድረግ ያለብን እንደሆኑ እንረዳለን፡፡ ሁለቱን እንዳናቀያይር በዝርዝር ማየቱ ጥሩ ነው፡፡ ( ታክሲ ግፊያ ላይ አንድ ሰው ቸኩሎ ረግጦን ታክሲ ውስጥ ሲገባና ሞባይላችንን ለመውሰድ ኪሳችን ውስጥ ሲገባ የምናደርጋቸው ነገሮች ይለያያሉ፡፡) 3. እንቅስቃሴ ማድረግ- ንዴት አእምሯዊ ስሜት የሆነውን ያክል አካላዊ መገለጫዎችም አሉት፡፡ እጃችን ይጨበጣል፤ ሰውነታችን ይወጣጠራል፡፡ ይህንን አካላዊ ውጥረት ለማርገብ አካላዊ እንቅስቃሴ...