Skip to main content

Featured Post

አስፐርገር ሲንድረም (Asperger syndrome)

The big bang theory ላይ የተሳለው ገፀ ባህሪ ሼልደን ኩፐር ለአስፐርገር  ሲንድረም ጥሩ ማሳያ ይሆናል፡፡ እናቱ ሁለቴ የአእምሮ ሀኪም ጋር ወስዳው ምንም የአእምሮ እክል የለብህም ቢባልም የሚያሳያቸው ፀባዮች አስፐርገር ሲንድረም እንዳለበት ይጠቁማሉ፡፡ አስፐርገር ሲንድረም ሰዎች አለምን የሚያዩበትን መንገድ እንዲሁም ከሰው ጋር የሚኖራቸውን ግንኙኘት የሚለውጥ ከኦቲዝም ህብር ህመሞች አንዱ ነው፡፡ እንደሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች የሌሎች ሰዎችን ስሜት ለመረዳት መቸገር፣ ለውጥ አለመፈለግ፣ ተመሳሳይ ነገሮችን ደጋግሞ መስራት ይታይባቸዋል፡፡ ከሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች በተሻለ የቋንቋ ክህሎታቸው እና አጠቃላይ የመገንዘብ /የመረዳት ችሎታቸው (ማህበራዊ ግንኙነትን ሳይጨምር) ጥሩ ነው፡፡ የተሻለ የመገንዘብና የንግግር ችሎታ ቢኖራቸውም ቋንቋን ሚረዱበት መንገድ የተለየ ነው፡፡ በተለይም ሽሙጥ፣ ስላቅን ለመረዳት ይቸገራሉ፡፡ ምሳሌያዊ አነጋገሮችን እንደወረደ በጥሬው ነው የሚረዱት፡፡ አስፐርገር መገለጫው ከሰው ሰው ስለሚለያይ መኖሩን በቀላሉ ለመለየት ያስቸግራል፡፡ህምናው በዋናነት ቶሎ መለየትና የማህበራዊ ክህሎት ስልጠና ነው፡፡ መልካም ጊዜ! ዶ/ር ዮናስ ላቀው

የአእምሮ ህመም ላለበት ሰው ማለት የሌለብን ነገሮች

ሰዎች "የአእምሮ ህመም አለብኝ፡፡"ወይም " ህክምና እከታተላለሁ::"ለማለት ይፈራሉ፡፡ በአብዛኛው ሰዎች በተለየ መንገድ እንዳያዩአቸው፤ ጥሩ ያልሆኑ ንግግሮች እንዳይናገሩ በመፍራት ነው፡፡ ተገቢ ያልሆነ ንግግር የሰዉን ስሜት የመጉዳት ሀይል አለው፡፡ የበለጠ የሚጎዳው ግን ቅርብ የሆኑና የምንወዳቸው ሰዎች ንግግር ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ባለማወቅ ወይም ሊያግዙ በማሰብ ሊሆን ይችላል፡፡ የምንናገረው ነገር ትልቅ ልዩነት ይፈጥራል፡ የማቅናት ወይም የመስበር፣ የመርዳት ወይም የመጉዳት፡፡የአእምሮ ህመም ላለበት ሰው ማለት የሌሉብን ነገሮች፦
 
እራስህን ነው የምታጨናንቀው፡፡
 
መጀመሪያ መጨናነቅ በአብዛኛው የእእምሮ ህመም መንስኤ ሳይሆን ውጤት ነው፡፡ በመቀጠል ደግሞ ማንም ሰው ፈልጎ ራሱን ሊያጨናንቅ አይችልም፡፡ ስለዚህ "እራስህን አታጨናንቅ" ማለት በህመም ውስጥ ያለ ሰው ላይ ትችት እንደመሰንዘር ነው፡፡
እንደውም ተመስገን በል ስንት ____ያጣ አለ፡፡
ባዶ ቦታው ላይ የተለያዩ ቃላት ተሞልቶበት በሀገራችን በብዛት የተለመደ ማፅናኛ ነው፡፡ ወደ ታች የሚደረግ ማህበራዊ ንፅፅር (downward social comparison)፡፡ ከኛ የባሰ ሁኔታ ውስጥ ሌሎች ሰዎች መኖራቸው ያለንበትን ሁኔታ ቀላል አያደርገውም፡፡ ስለ አለን ነገር ማመስገን ለአእምሮ ጤና አስፈላጊ ነው፡፡ ነገር ግን ምስጋናችን ከኛ የባሰ ሰው ስላላ መሆን የለበትም፡፡ በዛ ላይ ህመም ውድድር አይደለም፡፡ ከዛ ይልቅ የአእምሮ ህመም ያለበት ሰው የሚሰማውን ስሜት ለመረዳት መሞከር ጥሩ ነው፡፡
 
መድሃኒቱ ነው እንደዚህ የሚያደርግህ/ሽ
 
የአእምሮ ህክምና መድሀኒቶች እንደማንኛውም መድሀኒት የጎንዮሽ ጉዳት አላቸው፡፡ በአንፃሩ መድሃኒቶቹ ብዙ ሰዎችን ጥሩ እንቅልፍ የሚተኙ ፣ስራቸውን በደንብ መስራት የሚችሉ፣ትምህርታቸውን የጨረሱ፣ትዳራቸው ያልፈረሰ እንዲሆኑ ያግዛሉ፡፡ ስለ አእምሮ ህመምና ስለመድሃኒቶቹ በቂ እውቀት ሳይኖር በድፍረት "መድሃኒቱ ነው እንደዚህ የሚያደርግህ/ሽ፡፡ " ማለት አለማወቅ ነው፡፡ (ስለመድሃኒቶቹ የጎንዮሽ ጉዳት በቀጣይ ፅሁፍ ላይ ይቀርባል፡፡) የቅርባችን ሰዎች ትክክል ያልሆነ መድሃኒት እየወሰዱ ከመሰለን በእርጋታ ከነሱና ከሀኪም ጋር መነጋገሩ የተሻለ አማራጭ ነው፡፡
 
ቀላል አድርገህ እየው
 
እንቅልፍ ማጣት፣ ቀኑን ሙሉ እየተከፉ መዋል፣ እራስን ስለማጥፋት ማሰብ ቀላል አይደለም፡፡ ነገሮችን አጋንኖ ማየት ትክከል ያልሆነውን ያህል በጣም አቅልሎ ማየትም ስህተት ነው፡፡"ቀላል አድርገህ እየው፡፡"ልንባል እንችላለን፡፡ የመናገሩን ያህል ቀላል አይደለም፡፡ ድብርት ወይም ጭንቀት የአእምሮ ህመም እንጂ ቀላሉን ነገር ከባድ አድርገን ለማየት በመምረጣችን የሚመጣ ነገር አይደለም፡፡
በዋናነት የሚስፈልገው በግለሰባዊ አስተያት ላይ የተመሰረተ መፍትሄ ሳይሆን የሚያዳምጥ ጆሮ፤ ለመረዳት የሚሞክር ልብና ተገቢው ህክምና ነው፡፡ ከራሳችን ተሞክሮ ወይም ከዚህ በፊት ካጋጠሙን ሰዎች በመነሳት አስተያየት መስጠት ቀላል ነው፡፡ ቃላት ሀይል እንዳላቸው መዘንጋት የለብንም፡፡ የማቅናት ወይም የመስበር፣ የመርዳት ወይም የመጉዳት፡፡ስለዚህ የምንናገረውን መመዘኑ አስፈላጊ ነው፡፡
 
የአእምሮ ህመም ያለበት ሰው እንደማንኛውም ሰው ህልም፣ተስፋ፣ፍላጎት አለው፡፡ የተለየ አዘኔታ ወይም ትችት ሳይሆን እንደማንኛውም ሰው ፍቅርና አክብሮት ነው የሚያስፈልገው፡፡

Comments

Popular posts from this blog

አራቱ የልጅ አስተዳደግ አይነቶች (Parenting styles)

ልጆች የሚያድጉበት መንገድ ከፍ ሲሉ ከሰው ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት፣ የፍቅር ጓደኛ ምርጫ፣ ስኬት፣ በራስ መተማመን ላይ ትልቅ ሚና አለው፡፡ በተጨማሪም ከሴክስ፣ከገንዘብና ከአማች ቀጥሎ ትዳር ውስጥ አለመግባባት የሚፈጥረው የልጆች አስተዳደግ ነው፡፡ እንደ የስነ-ነልቦና ባለሞያዎች ወላጆች ልጆቻቸውን የሚያሳድጉባቸው መንገዶች በአራት ይከፈላሉ፡፡     አምባገነን (ኮስታራ) ፦ ይህ አይነት የልጅ አስተዳደግ በአለማችን በይበልጥ ደግሞ በሀገራችን ለረጅም ጊዜ የነበረ የማሳደጊያ መንገድ ነው፡፡ ከእናቶች ይልቅ ደግሞ አባቶች ላይ ይስተዋላል፡፡ እነዚህ ወላጆች ልጆቻቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው 'ኮስተር' ብለው ይነግሩና ልጆች 'ወለም ዘለም' ሳይሉ እንዲከተሉ ይጠብቃሉ፡፡ እንደዚህ የሚያድጉ ልጆች በአብዛኛው ስኬታማ ለመሆንና 'ትክክል' የሆኑ ነገሮችን ለማድረግ የሚጣጣሩ ሲሆኑ አዲስ ነገር ለመሞከር ወይም ያልተለመደ ስራ ለመስራት ይከብዳቸዋል፡፡ አንዳንዶቹ ከቤተሰብ ሲርቁ የማያምኑባቸውን ነገሮች ለማድረግ ይገፋፋሉ፡፡   የሚያሞላቅቁ (ሁሉንም የሚፈቀዱ)፦ ይሄ የልጅ አስተዳደግ በቅርብ የተጀመረ ሲሆን በከተማዎች በጣም እየተስፋፋ የመጣ አይነት ነው፡፡ እነዚህ ወላጆች ልጆቻቸው ያለ ገደብ እንደፈለጉ አንዲሆኑ ይፈቀዳሉ፡፡ ልጆቻቸው ያለ ከልካይና ያለ ገደብ እንደልባቸው እንዲሆኑ ከመፍቀድ ውጪ ምን ማድረግ እንዳለባቸው አይነግሯቸውም፡፡ ልጆቻቸው እስከፈለጉ ድረስ ከቤተሰቡ አቅም በላይ ቢሆንም እንኳ ለማሟላት ይጣጣራሉ፡፡እንደዚህ የሚያድጉ ልጆች ከቤት ውጭ እንደፈለጉ መሆን ስለማይችሉ ጭንቀት ይሰማቸዋል፡፡ የተወሰኑት ለምንም ነገር ሀላፊነት የማይሰማቸው ይሆናሉ፡፡   ግድ የለሽ፦ እነዚህ ወላ...

ምቀኝነት

ምቀኝነት አንድ ሰው እንዲኖረው የሚፈልገውን ችሎታ፣ ስኬት፣ ንብረት...ወዘተ ሌላ ሰው ሲኖረው የሚፈጠር ስሜት ሲሆን መሰረታዊ ከሆኑት ስሜቶቾ አንጻር ሲታይ የንዴትና የሀዘን ድብልቅ ነው፡፡ ሌላ ሰው የተሻለ ነገር ሲሰራ ወይም ሲኖረው ሁለት አይነት ስሜት ሊፈጥር ይችላል፡፡ አድናቆት ወይም ምቀኝነት፡፡ አድናቆት የሌላውን መሻል በትህትና መቀበል ሲሆን፤ ምቀኝነት በንዴት ላለመቀበል መሞከር ነው፡፡ ማን ማንን ይመቀኛል? ሰዎች የሚመቀኙት ከእነሱ ጋር ተቀራራቢ ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎችን ነው፡፡ ጓደኛ፣ ጎረቤት፣ የስራ ባልደረባ ...ወዘተ፡፡ ጫማህን የሚጠርገው ሊስትሮ አንተ የተሻለ ኑሮ ስራ ስላለህ ምቀኝነት አይሰማውም፡፡ ይልቁንም አጠገቡ ያለ ሌላ ሊስትሮ የተሻለ ገንዘብ ሲያገኝ ነው ምቀኝነት የሚሰማው፡፡ ጎረቤትህ የተሻለ ቤት ስትሰራ ምቀኝነት ይሰማው ይሆናል እንጂ አላሙዲን አዲስ ህንፃ ቢሰራ ምንም ስሜት አይፈጥርበትም፡፡ በአጠቃላይ ምቀኛ ከሩቅ አይመጣም፡፡   ምቀኝነት ወይስ ቅናት? አንዳንድ ሰዎች ሁለቱን ሲያቀያይሩ ይስተዋላል፡፡ ነገር ግን የተለያዩ ስሜቶች ናቸው፡፡ ቅናት ቦታ የምንሰጠው ነገር እንዳይወሰድብን ስንፈራ የሚፈጠር ስሜት ሲሆን እንዳይወሰድ የምንፈልገውን ነገር ለመጠበቅ ጥረት እንድናደርግ የሚገፋፋ ነው፡፡ በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ሲፈጠር ሰዎች ረጅም (አንዳንድ ጊዜ ከልክ ያለፈ) ርቀት እንዲሄዱ ያደርጋል፡፡ ምቀኝነት የሚፈጠረው አንድ ሰው ቢኖረው የሚመኘውን (ነገር ግን የሌለውን) ሌላ ሰው ሲኖረው የሚፈጠር ሲሆን ልዩነቱን ለማጥበብ ሌላውን ካለበት ለማውረድ ወይም ራስን ከፍ ለማድረግ እንዲጣጣር ይገፋፋል፡፡ "አላውቃትም እንዴ እንዴት እንደነበረች..." "እኔ ገንዘብ ሰጥቼው አይደል ስራ የጀመረ...

ሴክስ የሌለበት ትዳር

ረጅም ጊዜ ትዳር ውስጥ የቆዩ ሰዎች የሆነ ጊዜ ላይ ለረጅም ጊዜ ያለ ሴክስ ሊቆዩ ይችላሉ፡፡ በፊት በየቀኑ ወይም በሁለት ቀን አንዴ የነበረው ቀስ በቀስ ወደ ሳምንታት ከዚያም ወደ ወራት ሊዘልቅ ይችላል፡፡ በጣም አልፎ አልፎ ወይም ምንም ሳያደርጉ ደስተኛ ሆነው የሚኖሩ የተወሰኑ ባለትዳሮች አሉ፡፡ የሚበልጡት ግን አንዳቸው ወይም ሁለቱም ደስተኛ ሳይሆኑ የሚከሰት ነው፡፡ ከአምስቱ የፍቅር ቋንቋዎች ለአካላዊ ንኪኪ ቦታ የሚሰጡ ሰዎች ለረጅም ጊዜ ሴክስ አለማድረግ የአለመፈለግ ስሜት ይፈጥርባቸዋል፡፡ (ስለ አምስቱ የፍቅር ቋንቋዎች ከዚህ በፊት ቀርቧል፡፡) የሚሰማቸውን ስሜትና ሀሳብ ለመግለፅ ሀፍረት ስለሚሰማቸው ዝም ይላሉ፡፡ ዝምታው ሁለቱም ተጣማሪዎች የየራሳቸውን ግምት እንዲወስዱ ያደርጋቸዋል፡፡ (አንዳንድ ጊዜ አደገኛ የሆኑ ግምቶችን) ይህ ደግሞ ደስተኛ አለመሆን፣ መነጫነጭ፣ እንደ ባልና ሚስት ሳይሆን እንደ ደባል መተያየት የመጨረሻ ደረጃ ሲደርስ ደግሞ ፍቺ ሊያስከትል ይችላል፡ የሴክስ ፍላጎት በጊዜና በሁኔታ ከፍ ዝቅ የሚል ነገር ነው፡፡ ብዙ ነገሮችም ይወስኑታል፦ እርግዝና፣ ልጅ መውለድ፣ የስራ ጫና፣ አካላዊ ጤንነት...ወዘተ፡፡ በግልፅ ፍላጎትን፣ ፍርሀት፣ ስጋትን መነጋገር ጥሩ ነው፡፡ ቢቻል ንግግሩ ከመኝታ ቤት ውጨ በተረጋጋ ሁኔታ ቢደረግ ይመረጣል፡፡( መኝታ ቤት ወይም ከሴክስ በኃላ የሚደረጉ ውይይቶች በስሜት የሚደረጉ ስለሚሆኑ ከመፍትሄ ይልቅ ስሜትን የሚጎዱ መወቃቀሶችን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡) መኝታ ቤት የሚኖረው መግባባት ከመኝታ ቤት ውጭ ያለውን መግባባት እንደሚወስነው ከመኝታ ውጭ ያለው መግባባት የመኝታ ቤቱን መግባባት ይጨምረዋል፡፡ በተቃራኒውም ደግሞ እውነት ነው፡፡ መልካም ጊዜ! ...

አዎንታዊ ስነ ልቦና (Positive Psychology)

የአእምሮ ህመምን ማከም እንደሚያስፈልገው ሁሉ የአእምሮ ጤናን ማጎልበት፣ የሰዎች ድክመት ላይ ከማተኮር ጥንካሬያቸው ላይ ማተኮር፣ ጥሩ ያልሆኑትን ለማቅናት የሚሞክረውን ያህል ምርጥ የሆኑትን አንዲያድጉ ማገዝ የአዎንታዊ ስነልቦና ትኩረቶች ናቸው፡፡ የሰው ልጆችን ኑሮ በተሟላ እና በተመጣጠነ መልኩ ለመረዳት ይሞክራል፡፡ "ሰዎች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች እንዴት መፍታት ይችላሉ?" ከሚለው መደበኛው የስነ ልቦና ሀሳብ በተቃራኒው የቆመ አይደለም፡፡ በአንጻሩ የተለመደውን ስነ ልቦና የሚያግዝና አድማሱን የሚያሰፋ ነው፡፡ ሰዎች ከውልደት እስከ ሞት የሚያልፉባቸውን ሂደቶች ያጠናል፡፡ ሰዎች መሆን የሚችሉትን 'ምርጡን እራሳቸውን' እንዲሆኑ እንዲሁም የሚያደርጓቸውን ነገሮች በተሻለ መንገድ ማድረግ እንዲችሉ ያግዛል፡፡ በህይወት ውስጥ ጥሩ ነገሮች እንዳሉ ሁሉ በዛው ልክ መጥፎ ነገሮችም አሉ፡፡ የአዎንታዊ ስነ ልቦና ዋነኛ እሳቤው 'ጥሩ ህይወት' ውጣ ውረድን ከማለፍና ችግሮችን ከመቋቋም ከፍ ያለ መሆን አለበት የሚል ነው፡፡ ሰዎች በራሳቸው መንገድ ደስተኛ የሚያደርጋቸውንና በህይወታቸው የሚሰማቸውን እርካታ የሚወስኑ ነገሮችን ሲጠየቁ የሚሰጧቸው ምላሾች በሚያስገርም ሁኔታ ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ ከአሜሪካ ሚሊየነሮች እስከ የህንድ ጎዳና ተዳዳሪዎች የሰጧቸው ምላሾች ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቀጥለው የተዘረዘሩት ዘር ፣ ፆታ፣ የትምህርት ደረጃ ሳይለዩ ከደስታና ከአእምሮ ጤንነት ጋር ከፍተኛ ተያያዥነት አላቸው፡፡   ** የጓደኞች መኖር   ** ትዳር   ** ተጫዋች መሆን   ** አመስጋኝ መሆን   ** ሀይማኖተኛ ሰው መሆን   ** መዝና...

ሁለት ውብ ታሪኮች ከአማኑኤል ሆስፒታል

አማኑኤል ሆስፒታል የሰው ድክመት፣ ውድቀት፣ ህመም ብቻ የሚሰማበት የሚመስላቸው ሰዎች አይጠፉም፡፡ ነገር ግን በየቀኑ የመነሳት፣ የጥንካሬ፣የፅናትና የፍቅር ውብ ታሪኮች ይስተናገዳሉ፡፡ ሁለቱ በዚህ ሳምንት ከገጠመኝ እነሆ፦   1) አማኑኤል የሴቶች ዋርድ የሀኪሞች ክፍል ተቀምጬ ካርድ ላይ እየፃፍኩ ነው፡፡ በሩ ገርበብ ብሏል፡፡ አንድ ታካሚ ከአልጋዋ ከነጋ አልተነሳችም፡፡ የደበራት ትመስላለች፡፡ ገርበብ ባለው በር ትታየኛለች፡፡ አንድ ወጣት ሴት ፍራፍሬ በፌስታል ይዛ ልትጠይቃት ትገባለች። አይኗ ብርት ብሎ ከአልጋዋ ወዲያው ተነሳች። ተቃቀፉ፡፡ በቀናት ውስጥ ያላየንባት ደስታ ውስጥ ሆና መጫወት ጀመሩ፡፡ ጠያቂዎን አውቃታለሁ፡፡ ከሳምንት በፊት እዚሁ ሆስፒታል እዚሁ ክፍል ተኝታ ነበር፡፡ ጓደኛዋን ልትጠይቅ መምጣቷ ነው፡፡ ተኝታ የምትታከመው ድንገት አቀረቀረች፡፡ አይኗን ሳታነሳ ጓደኛዋን "ግን የምንድን ይመስልሻል?" ብላ ጠየቀቻት፡፡ ጓደኛዋ እቅፍ አደረገቻት "እሱ የፈጣሪ ስራ ነው፡፡ እኛ ግን መድሀኒታችንን እንወስዳለን አለቻት፡፡"... አንድ የኩላሊት ጠጠር ቀዶጥገና ሀኪም "ሀኪሙ ጠጠሩን ያወጣል፤ የሚያድነው ግን አምላክ ነው፡፡" ያለው ትውስ አለኝ፡፡   2) ታካሚ ወንድሙን ይዞ ኦፒዲ ይገባል፡፡ መልካቸው በጣም ይለያያል፡፡ "እባካችሁ ተኝቶ ይታከም?" አለን፡፡ "ያልተለመደ ፀባይ ሲታይበት አከራዮቻችን ቤት እንድንለቅ ጠየቁን፡፡ ለትንሽ ጊዜ ቢተኛ?" አለን፡፡ "ቤተሰቦቻችሁ የት ናቸው?" ብዬ ጠየቅኩት፡፡ መልሱ ያልጠበቅኩት ነበር፡፡ "ከተለያየ ቤተሰብ ነው የመጣነው ግን ወንድሜ ነው፡፡ በማደጎ አብረን ነው ያደግ...