Skip to main content

Posts

Showing posts from February, 2018

Featured Post

አስፐርገር ሲንድረም (Asperger syndrome)

The big bang theory ላይ የተሳለው ገፀ ባህሪ ሼልደን ኩፐር ለአስፐርገር  ሲንድረም ጥሩ ማሳያ ይሆናል፡፡ እናቱ ሁለቴ የአእምሮ ሀኪም ጋር ወስዳው ምንም የአእምሮ እክል የለብህም ቢባልም የሚያሳያቸው ፀባዮች አስፐርገር ሲንድረም እንዳለበት ይጠቁማሉ፡፡ አስፐርገር ሲንድረም ሰዎች አለምን የሚያዩበትን መንገድ እንዲሁም ከሰው ጋር የሚኖራቸውን ግንኙኘት የሚለውጥ ከኦቲዝም ህብር ህመሞች አንዱ ነው፡፡ እንደሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች የሌሎች ሰዎችን ስሜት ለመረዳት መቸገር፣ ለውጥ አለመፈለግ፣ ተመሳሳይ ነገሮችን ደጋግሞ መስራት ይታይባቸዋል፡፡ ከሌሎች የኦቲዝም ህብር ህመሞች በተሻለ የቋንቋ ክህሎታቸው እና አጠቃላይ የመገንዘብ /የመረዳት ችሎታቸው (ማህበራዊ ግንኙነትን ሳይጨምር) ጥሩ ነው፡፡ የተሻለ የመገንዘብና የንግግር ችሎታ ቢኖራቸውም ቋንቋን ሚረዱበት መንገድ የተለየ ነው፡፡ በተለይም ሽሙጥ፣ ስላቅን ለመረዳት ይቸገራሉ፡፡ ምሳሌያዊ አነጋገሮችን እንደወረደ በጥሬው ነው የሚረዱት፡፡ አስፐርገር መገለጫው ከሰው ሰው ስለሚለያይ መኖሩን በቀላሉ ለመለየት ያስቸግራል፡፡ህምናው በዋናነት ቶሎ መለየትና የማህበራዊ ክህሎት ስልጠና ነው፡፡ መልካም ጊዜ! ዶ/ር ዮናስ ላቀው

የአእምሮ ህመም ላለበት ሰው ማለት የሌለብን ነገሮች

ሰዎች "የአእምሮ ህመም አለብኝ፡፡"ወይም " ህክምና እከታተላለሁ::"ለማለት ይፈራሉ፡፡ በአብዛኛው ሰዎች በተለየ መንገድ እንዳያዩአቸው፤ ጥሩ ያልሆኑ ንግግሮች እንዳይናገሩ በመፍራት ነው፡፡ ተገቢ ያልሆነ ንግግር የሰዉን ስሜት የመጉዳት ሀይል አለው፡፡ የበለጠ የሚጎዳው ግን ቅርብ የሆኑና የምንወዳቸው ሰዎች ንግግር ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ባለማወቅ ወይም ሊያግዙ በማሰብ ሊሆን ይችላል፡፡ የምንናገረው ነገር ትልቅ ልዩነት ይፈጥራል፡ የማቅናት ወይም የመስበር፣ የመርዳት ወይም የመጉዳት፡፡የአእምሮ ህመም ላለበት ሰው ማለት የሌሉብን ነገሮች፦   እራስህን ነው የምታጨናንቀው፡፡   መጀመሪያ መጨናነቅ በአብዛኛው የእእምሮ ህመም መንስኤ ሳይሆን ውጤት ነው፡፡ በመቀጠል ደግሞ ማንም ሰው ፈልጎ ራሱን ሊያጨናንቅ አይችልም፡፡ ስለዚህ "እራስህን አታጨናንቅ" ማለት በህመም ውስጥ ያለ ሰው ላይ ትችት እንደመሰንዘር ነው፡፡ እንደውም ተመስገን በል ስንት ____ያጣ አለ፡፡ ባዶ ቦታው ላይ የተለያዩ ቃላት ተሞልቶበት በሀገራችን በብዛት የተለመደ ማፅናኛ ነው፡፡ ወደ ታች የሚደረግ ማህበራዊ ንፅፅር (downward social comparison)፡፡ ከኛ የባሰ ሁኔታ ውስጥ ሌሎች ሰዎች መኖራቸው ያለንበትን ሁኔታ ቀላል አያደርገውም፡፡ ስለ አለን ነገር ማመስገን ለአእምሮ ጤና አስፈላጊ ነው፡፡ ነገር ግን ምስጋናችን ከኛ የባሰ ሰው ስላላ መሆን የለበትም፡፡ በዛ ላይ ህመም ውድድር አይደለም፡፡ ከዛ ይልቅ የአእምሮ ህመም ያለበት ሰው የሚሰማውን ስሜት ለመረዳት መሞከር ጥሩ ነው፡፡   መድሃኒቱ ነው እንደዚህ የሚያደርግህ/ሽ   የአእምሮ ህክምና መድሀኒቶች እንደማንኛውም መድሀኒት የጎንዮሽ ...

ሶሻል ፎቢያ (Social phobia)

ሶሻል ፎቢያ ያለባቸው ሰዎች ሌሎች ሰዎች ባሉበት ዘና ማለት አይቻሉም፡፡ ሌሎች ሰዎች የእነሱን ንግግር ወይም ድርጊት የሚገመግሙና የሚተቹ ስለሚመስላቸው ይፈራሉ፡፡ስህተት እንዳይሰሩና እንዳይዋረዱ ስለሚፈሩ ዘና ብለው እንደሚፈልጉት ከሰዎች ጋር መጫወት ይከብዳቸዋል ፡፡ አብዛኛው ሰው ካልለመደው ሰው ጋር ሲሆን የአለመመቸት ስሜት ይፈጠርበታል፡፡ ሶሻል ፍቢያ ሲሆን ግን ፍርሀቱ በጣም የበዛ ይሆናል፡፡ ሶሻል ፎቢያ ያለባቸው ሰዎች አብሯቸው ያሉ ሰዎች ሲጫወቱ ፣ሲስቁ ፣ሲያወሩ እነሱ መሣተፍ ስለማይችሉ ብቸኝነት ይሰማቸዋል፡፡ ብቻቸውን ግን አይደሉም፡፡ ከአስር ሰው አንዱ ተመሣሣይ ሁኔታ ውስጥ ነው፡፡ ነገ መንገድ ላይ ሲሄዱ አስር ሰዎች ይቁጠሩ ከዛ ውስጥ አንዱ ሶሻል ፍቢያ አለበት/አለባት፡፡ የሶሻል ፎቢያ ምልክቶች በጥቅቱ፦ -ከቤት ውጪ ምግብ ባይበሉ ይመርጣሉ፡፡ለብቻቸው ሬስቶራንት ገብተው፣ ባዶ ጠረጴዛ ፈልገው፣ 'ያ ሁሉ ሰው' እያያቸው መመገብ ይከብዳቸዋል፡፡ - ዝግጅቶች ላይ በግድ ነው የሚገኙት (እሱንም ከተገኙ!)-እስከቻሉት ድረስ ምክኒያት ፈጥረው ለመቅረት ይሞክራሉ፡፡ - በአብዛኛው የድካም ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ - ሰዎች ሲሰበሰቡ ከመጨነቅ ጋር ተያይዞ ልብ ቶሎ ቶሎ መምታት፣ ትንፋሽ ቁርጥ-ቁርጥ ማለት፣ ማላብ - ነገሮች እጅግ አስከፊ ሊሆኑ እንደሚችሉ በማሰብ መጨናነቅ ፣እንቅልፍ ማጣት - የፍቅር ቀጠሮች ላይ (በተለይየመጀመሪያዎቹ ላይ) ምን እንደሚባል አለማወቅ... ከላይ የተዘረዘሩትን ሶሻል ፎቢያ ያለባቸው ሰዎች ይረዱታል፡፡ ሌሎች ግን ቀለል አድርገው ሊያዩት ይችላሉ፡፡ ሶሻል ፎቢያ ተማሪዎች እውቀት እያላቸው ጥሩ ውጤት እንዳይኖራቸው፤ ሰራተኞች ችሎታ እያላቸው የሚገባቸውን እድገት እንዳያገኙ፣ እንዲሁም ለ...